Trendings

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ዙር የአመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ

የህልም ጉልበት፤ለእመርታዊ እድገት ‘!በሚል መሪ ሀሳብ 2ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ የአመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ በቦንጋ ማዕከል መካሄድ ጀምሯል። “የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ በሚሰጠው በዚህ ሁለተኛ ዙር ስልጠና በክልሉ 683 አመራሮች ተሳታፊ ይሆናሉ። በንድፈ ሀሳብና በነባራዊ እውነታዎች ተደግፎ በሚሰጠው በዚህ ስልጠና በየደረጃው ያለው አመራር ዓለም አቀፋዊ ፣ አህጉራዊ፣ ቀጠናዊና ሀገራዊ ፖለቲካዊ ፣…

Read More

ኮሚሽኑና የሐይማኖት ተቋማት በጋራ ለመሥራት ግብረ-ኃይል አዋቀሩ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና የሐይማኖት ተቋማት በቀጣይ በጋራ በሚሠሯቸው ተግባራት ላይ ግብረ-ኃይል በማቋቋም በትብብር ለመስራት ተስማሙ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሐይማኖት ተቋማትን ሚና እና ተሳትፎ በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ለማጎልበት ያለመ ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባላት እና በጉባዔው በአባልነት ያልተመዘገቡ የሐይማኖት ተቋማት መሳተፋቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡ የኮሚሽኑ ዋና…

Read More

“በብዙ የሀገራችን ክፍል እንደሚታየው የደቡብ ክልል በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገ ነው። በያዝነው የምርት ዘመን የፍራፍሬ እና አትክልት ምርት በተለየ ሁኔታ አጥጋቢ ሆኗል። 34.5 ሚሊዮን ኩንታል ፍራፍሬ እና 7.6 ኩንታል አትክልት ተመርቷል። ይኽን በደቡብ ክልል የታየ ስኬት በሌሎች ክልሎችም ለማስፋፋት የጋራ እድገት ለማስገኘት እና የምግብ ዋስትና ትልማችንን አሳክቶ ዘላቂ ልማትን በሚያረጋግጥ መልክ ጠንክረን መስራት ይገባል።”፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

+3 All reactions: 66

Read More

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መልካም ምኞታቸውን ገለጹ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ከፍተኛ አመራሮች ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሰራተኞች ለፕሬዚዳንቱ መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸውም ምኞታቸውን መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Read More

የአስተዳደር ወሰን ጥያቄዎች የህዝቦችን ወንድማማችነት በሚያጠናክር መልኩ እልባት እንደሚያገኝ ተገለፀ

የአስተዳደር ወሰን ጥያቄዎች የህዝቦችን ወንድማማችነት በሚያጠናክርና ዘላቂ ሰላምን ሊያሰፍን በሚችል መልኩ እልባት ለመስጠት እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ በስብሰባው፤ የማንነት አስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው 2017 በጀት ዓመት እቅድ፤ የወልቃይት፣ ራያና ጠለምት ጥያቄዎችን ለመመለስ ከአካባቢው መስተዳድርና ነዋሪዎች ጋር ውይይት በማካሄድ በአካባቢው ያለውን…

Read More

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን 4ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን ማካሄድ ጀመሯል፡፡ ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ቃለ ጉባዔውን መርምሮ በማጽደቅ ጉባኤውን ማካሄድ የቀጠለ መሆኑም ተመላክቷል። ምክር ቤቱ በጉባኤው ያጸደቃቸውን ሌሎች አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍባቸው…

Read More

ፕሬዚዳንት ታዬ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ21 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን ገለጹ

በ2016 በጀት ዓመት በተለያዩ መስኮች ከ21 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንት ታዬ ለሁለቱ የፌዴራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌዴራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ አቅርበዋል፡፡ በንግግራቸውም አጠቃላይ…

Read More