


የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን 4ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን ማካሄድ ጀመሯል፡፡
ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ቃለ ጉባዔውን መርምሮ በማጽደቅ ጉባኤውን ማካሄድ የቀጠለ መሆኑም ተመላክቷል።
ምክር ቤቱ በጉባኤው ያጸደቃቸውን ሌሎች አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍባቸው እንደሚጠበቅም የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
