





የህልም ጉልበት፤ለእመርታዊ እድገት ‘!በሚል መሪ ሀሳብ 2ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ የአመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ በቦንጋ ማዕከል መካሄድ ጀምሯል።
“የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ በሚሰጠው በዚህ ሁለተኛ ዙር ስልጠና በክልሉ 683 አመራሮች ተሳታፊ ይሆናሉ።
በንድፈ ሀሳብና በነባራዊ እውነታዎች ተደግፎ በሚሰጠው በዚህ ስልጠና በየደረጃው ያለው አመራር ዓለም አቀፋዊ ፣ አህጉራዊ፣ ቀጠናዊና ሀገራዊ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ሁኔታዎችን ተገንዝቦ ወቅቱን የዋጀና ውጤታማ አመራር ለመስጠት ያስችለዋል።
ስልጠናው ሀገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ከግብ ለማድረስ አመራሩ በአሰተሰሰብ ፣ በእውቀት፣ በክህሎትና በሥነ ምግባር ጎልብቶ የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃትና በቁርጠኝነት ለመወጣት የሚያስችለውን አቅም ያዳብራል ተብሎ ይጠበቃል።
በስልጠናው የክልል ፣የዞን የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች የጀመረ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ስልጠና የተሳተፉ አመራሮች በስልጠናው አስተባባሪነት ፣ በአስልጣኝነትና በአወያይነት የሚሳተፉ ይሆናል።
የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ በሚሰጠው በዚህ ሁለተኛ ዙር ስልጠና ከፌደራል እስከ ቀበሌ ደረጃ የሚገኙ 24,851 አመራሮች ተሳታፊ ይሆናሉ።
