‹‹የገዢ ትርክት ዕሳቤ በመደመር መንገድ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው››፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

የገዢ ትርክት ዕሳቤ በመደመር መንገድ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄ ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽና ማብራሪ፤ ገዢ ትርክት አሰባሳቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ገዢ ትርክት ውቅሮች ህገ መንግስታዊ፣ ሕብረብሔራዊ፣ ልማታዊ፣ የመማርና የጋራ ሕልም ውቅር አለው። በውስጡ እኩልነት፣ ዴሞክትራሲና ፍትህ አለ። ይህንን በመቀበል ለጋራ እድገት መሥራትም ያካትታል ነው ያሉት።

በገዢ ትርክት ኃይል ያሰባስባል የተሰበሰበው ኃይልም ለልማት ይውላልም ነው ያሉት፡፡

መደመር ማለት ትናንትናና ዛሬን፤ ዛሬና ነገን ማስተሳሰር ማለት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከትናንት ጠቃሚ ትርክቶች ብቻ በመውሰድ ተስፋን መሰነቅ ይገባል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *