ባለፉት ዓመታት 249 ሺህ ቤቶች ለአቅመ ደካማ ዜጎች ተላልፈዋል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

መንግስት ባለሐብቶችን በማስተባበር ባከናወነው ስራ ባለፉት ዓመታት 249 ሺህ ቤቶችን በመስራት እና በማደስ ለአቅመ ደካማ ዜጎች መተላለፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ለአቅመ ደካማ ዜጎች ቤት ሰርቶ መስጠት ልምምድ ያደረገ የግል ባለሐብት እየተፈጠረ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህ ተግባር ውስጥ የተሳተፉ ባለሐብቶች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

የኑሮ ውድነቱ እጅ አጠር ዜጎች ላይ ጫና እንዳይፈጥር በተያዘው ዓመት መንግስት ከ300 እስከ 400 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት መመደቡን ተናግረዋል፡፡

በማዕድ ማጋራት፣ በትምህርት ቤት ምገባ እና እሁድ ገበያ መንግስት አቅመ ደካሞችን ለማገዝ የሚያደርገው ጥረት አካል መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *