ኮንታና ዳውሮ፤ ድንቅ የተፈጥሮ እጅ ሥራ!
መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም ማለዳ ከአዲስ አበባ የተነሳው የጋዜጠኞች ቡድን ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሚያደርገውን ጉዞ ጀምሯል። በኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና በቱሪዝም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተዘጋጀው የሚዲያዎች ጉዞ፤ የቱሪስት መዳረሻዎችን ማስተዋወቅ ዓላማው አድርጎ ወሊሶን ተሻግሮ፣ ወልቂጤን አቋርጦ፣ ጅማ አረፍ ብሎ በአመያ አዳሩን አድርጓል። የጋዜጠኞቹ ቡድን በማግስቱ ጥቅምት 17 ደግሞ የግማሽ ቀን ጉዞ አድርጎ…
