
ብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ‘ከቃል እስከ ባህል’ በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት ያካሂዳል።
የፓርቲው ዓለም አቀፍና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው የፓርቲው 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በርካታ ውሳኔዎች ይወሰናሉ።
በተጨማሪም ወሳኝ አቅጣጫዎች የሚተላለፍበት እንደሚሆን አመልክተዋል።
በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ እሁድ በሚካሄደው ጉባኤ ከፓርቲው አባላትና አመራሮች በተጨማሪ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ያለድምፅ ይሳተፋሉ።
እንዲሁም ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል።
