ሰበር ዜና

Spread the love

ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።

ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ክቡር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) እጅግ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መርጧቸዋል። ተመራጩ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

በተያያዘ ዜና ጉባኤው ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና ክቡር አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚደንቶች አድርጎ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መርጧል።

ሁለቱ ምክትል ፕሬዚደንቶች በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *