






የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከኢፌዴሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከ አመራሮች ጋር የክልሉን የከተማ ልማት ስራዎች ላይ ያተኮረ ዉይይትላይ በጽህፈት ቤታቸው አድርገዋል፡፡
የኢፌዲሪ ከተማ መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ የከተማ መሬት በምዳባና በጨረታ በማስተላለፍ ሰነድ አልባ የከተማ መሬቶችን ወደ ህጋዊ መስመር ከማስገባት ጥሩ ጅምር ስራዎች መኖራቸውን ገልጸው ለቀጣይነቱ የፖለቲካ አመራር ቁርጠኝነት ይጠይቃል ነው ያሉት ፡፡
የሱፐርቪዥን ቡዱኑ በአጠቃላይ በክልሉ የገጠርና ከተማ ኮሪደር ተግባራት ጥሩ ጅምር ስራዎች አይተናል ያሉ ሲሆን ከከተማ ጽደት አንፃር የከተማ ቆሻሻ መልሶ ከመጠቀም አንፃር በቀጣይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር የማታለም ቸኮል የከተሞች ኮሪደር ልማትን የተሻለ ለማድረግ ህብረተሰቡንና ባለሃብቶችን በማሳተፍ የተጀመሩ ጥሩ ጅምር ስራዎች መኖራቸውን ገልጸው ይህንን አጠናክሮ ማስቀጠል የሚያስፈልግ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የከተሞች አረንጓዴ ሽፋንን ለማሳደግ ለከተማ እንደ ክልል ከተማ ልማትና ኮንሰትራክሽን ቢሮ ሰፊ ስራዎች እየተሰራ ነው ቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም በውይይቱ መድረኩ ላይ አብራርተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፤ የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን በየወቅቱ በክልላችን በተጨባጭ መሬት ላይ ያሉ ተግባራትን ምልከታ በማድረግ በየጊዜው የሚሰጠው ግብረ መልስ ለክልሉ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ክልል የኮሪደር ልማት ስራ ዘግይቶ የተጀመረ ቢሆንም ከሌሎች ከተሞች ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ለማጠናቀቅ የተጀመሩ በርካታ ጥሩ ጅምር ስራዎች መኖራቸውንና ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ከከተማ ገቢ አንፃር በከተሞች አካባቢ በርካታ የገቢ መሠረቶች መኖራቸውን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ በሚፈለገው መልኩ ሰብስቦ ልማት ላይ ከማዋል አንፃር በቂ አይደለም በቀጣይ ከተሞች በልዩ ትኩረት መስራት የሚፈልግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ከከተማ ማዘጋጀ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን በሁሉም ከተሞች የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሂሩት ዮሐንስ፤ በክልሉ ኮሪደር ልማት ስራ በሚመለከት ጥሩ ጅምር ስራዎች ያለው ቢሆንም ባለሀብቱንና ህብረተሰቡን እንዲሁም የተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅት በኮሪደር ልማት ስራው ማሳተፍ አጠናክሮ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
ከመሠረተ ልማት አኳያ የተጀመሩ ጥሩ ስራዎች ያሉ ቢሆንም አሁንም በመንገድ መሠረተ ልማት ዘርፍ ያለውን ችግር በመለየት ትኩረት ተሰጥቶ መስራት የሚጠይቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
