
“ባለቤት አለኝ፤ አሁን እንዴት ነው ከባለቤቴ ጋር ሰላም የምናገኘው መተማመንስ የሚኖረን?” – ብርቱካን ተመስገን
ሀሰተኛ ድራማ የተሠራባት ብርቱካን ተመስገን ቤተሰቦቻቸው ጋር ሄደው በአካባቢው ባህል መሰረት ትዳር እንደመሰረተች ራሷም ባለቤቷም ምሥክርነት ሰጥተዋል።
በጋብቻዋም የሁለት ዓመት ልጅ እንዳፈራች እና በመልካም ሁኔታ ስትኖር እንደነበር ጎረቤቶቿን ጨምሮ ሁሉም ምሥክርነት ሰጥተዋል።
ብርቱካን ከመዓዛ መሐመድ ጋር በስልክ ባደረገችው ንግግር ያስጨነቃት እንዴት ከባለቤቷ ጋር ተመልሳ እንደምትኖር ነው።
ባሏን ያገባቸው በድንግልና እንደሆነ የምታወሳው ብርቱካን፤ አሁን እንዴት ባሏ የድሮ ማንነቷን እንደሚቀበል እና ቀጣይ ምን ዓይነት ሕይወት ሊኖራት እንደሚችል ትጠይቃለች።
ይህን ሁሉ እንድትጠይቅ ያደረጋት ጉዳይን የሚያረጋግጠው የጋብቻዋ ሁኔታ በምሥክር ወረቀት የተረጋገጠ እንደሆነ መረጃ ተገኝቷል።
ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆነው ከወሳኝ ኩነት ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም የተሰጣቸው የጋብቻ ምሥክር ወረቀት ነው ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
