



በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቅ/ጽ/ቤት የ2017 ዓ/ም የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በአማያ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የአፈፃፀም ግምገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በብልጽግና ፓርቲ መሪነት በክልሉ መጠነ ሰፊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ፍቅሬ፥ ፓርቲው በክልሉ የህዝቡን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን በማድመጥ ደረጃ በደረጃ ምላሽ እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የአፈጻጸም ግምገማ መድረኩ፥ በፓርቲው ተቀርጾ የወረዱ ኢንሼቲቮች ውጤታማነት ከህዝብ ተጠቃሚነት አኳያ በጥልቀት በመገምገም ለቀጣይ ተልዕኮ የላቀ ዝግጁነት የጋራ አቋም የሚያዝበት እንደሆነም ነው አቶ ፍቅሬ ያስገነዘቡት።
ጠንካራ ፓርቲ፤ ለጠንካራ መንግሥት መሠረት በመሆኑ በዚህም ረገድ በመዋቅር መካከል የተሰሩ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር ለሌሎች በማካፈል ወጥነት ያለውን አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደሚገባም የገለጹት አቶ ፍቅሬ የፓርቲው ተግባራት ከሂዴት በመውጣት በውጤቱ የሚለኩ መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።
የፓርቲ አደረጃጀቶችን በተልዕኮው መፈተሽ፤ አመራርና አባሉ በአንድ ጊዜ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እንዲፈጽሙ ማስቻል እንደሚገባ የገለጹት አቶ ፍቅሬ የፓርቲውን ተልዕኮ በተገቢው በመፈጸም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
በ3ኛ ሩብ ዓመቱ በጥንካሬ የታዩ ተግባራትን ማስቀጠል እና በእጥረት የታዩ አፈጻጸሞችን ፈጥኖ በማረም በቀሪ አጭር ጊዜያት የላቀ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደሚገባም ነው ኃላፊው የጠቆሙት።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በዞኑ አጠቃላይ በፓርቲ ተግባራት የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን የጠቆሙት የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ፥ በፓርቲው ተቀርጾ የወረዱ ኢንሼቲቮችንና የንቅናቄው አጀንዳዎች በተሻለ መልኩ መፈጸም መቻሉን አብራርተዋል።
ከአጠቃላይ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ስራዎች በተጨማሪ በፓርቲው የወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶችን በማጠንከር ከፖለቲካ ተሳትፎ ባሻገር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሳደግ መቻሉንም እንዲሁ።
ጠንካራ የህዝብ ተሳትፎ በማከል ተግባራት በውጤት የታጀበ እንዲሆን በትኩረት መከናወኑን ያብራሩት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ታከለ የአፈጻጸም መደረኩ ለቀጣይ ተልዕኮዎች ትምህርት የሚወሰድበት እንደሆነ ተናግረዋል።
በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዘርፍ ኃላፊዎች፣ የዞን፣የወረዳ አመራሮች እና የክልል ማዕከል የብልጽግና ኅብረት ሰብሳቢዎች የተገኙ ሲሆን ዝርዝር የአፈጻጸም ሪፓርት እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን ቀጣይ በቀረበው ሪፖርተር ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።
በዕድገቱ በዛብህ
