ቆይታ ከእኛ ጋር!

Spread the love


ፍርድ ቤቶች ለዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር፣ የህግ የበላይነትን ማስፈን እና በክልሉም ሆነ በሀገሪቱ የተፋጠነ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት በሚደረገዉ ጥረት የዳኝነት አካላት ሚና ከፍተኛ ነው ፡፡


ፍርድ ቤቶች ነጻ እና ገለልተኛ ሆነዉ  ህግ በመተርጎም የዳኝነት አገልግሎት እንዲሰጡ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ በመሆኑም የመንግሥት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ፤ እንዲሁም የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ግንባታ ዕቅዶች እንዲሳኩ ፍርድ ቤቶች የራሳቸዉ ድርሻ ያላቸዉ እንደመሆኑ መጠን በየደረጃዉ የሚገኙ የክልሉ ፍርድ ቤቶች በክልሉ ህገ-መንግስት እና በሌሎች ህጎች በተሰጣቸው ሕግን የመተርጎም ሥልጣንን መሠረት በማድረግ የዜጎች ሰብዓዊና ዳሞክራሲያዊ፣ መብቶች እንዲከበሩ ለክልሉ ልማትና ዕድገት የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት እየተወጡ ይገኛሉ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በስድስት ዞኖች ሥር በሚገኙ ሰባት ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች እና በሥራቸዉ የሚገኙ 41 የወረዳ እና 17 የከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶችን ይዞ በወንጀልና በፍትኃብሔር ጉዳዮች በመጀመሪያ ደረጃ ክስ፣ በይግባኝ እና በሰበር የክልሉ ማህበረሰብ የዳኝነት አገልግሎት እንድያገኝ በክልሉ የዳኝነት አገልግሎት ቅልጥፍና እና ዉጤታማነት እንዲሻሻል ትኩረት በመስጠት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
እኛም ባለፉት 9 ወራት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅዶ ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ከሆኑት አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም ጋር ቆይታ አድርገን ያሰናዳነውን ዝግጅት ለንባብ አብቅተናል መልካም ንባብ !
መ/ኮ፣ ስምዎንና ኃላፊነትዎን  ቢገልጹልኝ
አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም ፣ አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት
መ/ኮ፣ በ2017 በጀት ዓመት የተጣሉ ዋና ዋና ግቦች ምንድን ናቸው ? ቢገልጹልኝ?
አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም ፣  የዳኝነት አገልግሎት ቅልጥፍና ፡-ዉጤታማነት፣ተደራሽነት፣ነጻነት፣ገለልተኛነትና ተጠያቂነት  ማሻሻል አንጻር በሁሉም ደረጃ ፍርድ ቤቶች  እንደ ዋና ዋና ግብ ተይዘዉ ትኩረት በማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ፡፡
መ/ኮ፣ በእነዚህ ዋና ዋና ግቦች የተከናወኑ አብነት የሆኑ ተግባራትን ቢያብራሩ?
አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም ፣ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና ከዉጤታማነት አፈጻጸም አንጻር በሁሉም ደረጃ ባሉ ፍርድ ቤቶች በ2017 በጀት ዓመት በ9ወር ዉስጥ ካለፈው በጀት ዓመት የተሻገሩ 529 ወንጀል እና 1420 ፍ/ሄር በድምር 1‚949 መዝገቦች፤አዲስ የቀረበ ወንጀል 16‚012 እና ፍ/ሄር 27,173 በድምሩ 43,185 መዝገቦች የቀረበ ሲሆን፣ በአጠቃሊይ 16,541 ወንጀል እና 28,593 ፍ/ሄር በድምሩ 45,134 መዝገቦች የቀረቡ ስሆን ከቀረቡ መዝገቦች መካከል ወንጀል 15‚628 ፍ/ሔር 26‚506 በድምሩ 42,134 መዝገቦች ላይ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ 915 ወንጀል እና 2085 ፍትኃ ብሄር በድምሩ 3‚000 መዝገቦች ወደ ቀጣይ ሩብ ዓመት ተሸጋግረዋል፡፡ የ9ወር አፈጻጸም ከቀረቡ መዝገቦች አንጻር 93.3 ፐርሰንት መሆኑን አፈጻጸሙ ያሳያል፡፡
ከዳኝነት አገልግሎት ዉጤታማነት አንጻር የሚሻሩ ውሳኔዎችን የመቀነስ ሥራ አፈጻጸም በበጀት ዓመቱ በይግባኝ የሚሻሩ ውሳኔዎችን በ99.1% ለማድረስ ታቅዶ በአጠቃሊይ ውሳኔ ከተሰጠባቸው 42,134 መዝገቦች መካከል በየደረጃዉ ባሉ ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች  3579 መዝገቦች ላይ ይግባኝ ተጠይቆ ውጤቱ የታወቀው 2168 ሲሆን ከዚህ ውስጥ የፀናው 1701 በመሆኑ አፈፃፀሙ 78.45% ነው፡፡ ቀሪ መዝገቦች በሂደት ላይ ቢሆኑም ይህ ግብ በቀጣይ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራ እንደሆነ ያመላክታል፡፡
በአማራጭ የሙግት መፍቻ መንገድ በተለይም በዕርቅና ድርድር በህግ በተፈቀደ ጉዳዮች እልባት በመስጠት የተከራካሪ ወገኖችን ጊዜ፣ወጪና ጉልበት ከመቆጠብም ባለፈ በተከራካሪዎች መካከል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በዚህ ረገድ መዝገቦች ከመቋጨት አንፃር በ9ወሩ በየደረጃዉ ባለ ፍርድ ቤቶች ከሚወሰኑ መዝገቦች ውስጥ 6164  መዝገቦች በዕርቅና ድርድር ለመጨረስ ታቅዶ 3838 መዝገቦች የተወሰኑ ሲሆን አፈፃፀሙ 62.26% ነው፡፡ ይህ ያልተሳካዉ እርቅ በተከራካሪ ወገኖች የሚፈጸም በመሆኑ  ወደ ፍርድ ቤት ከመጡ በኋላ በእርቅ እንድጨርሱ ስጠየቁ ፈቃደኝነታቸዉ አናሳ ስለሆነ ነዉ፡፡
መ/ኮ፡- ከተደራሽነት አንጻር የተሰሩ ስራዎች ይኖራሉ ?
አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም ፡-አዎን በሚገባ እየተሰራበት ይገኛል ለአብነትም ፡-የተዘዋዋሪ ችሎት ሥራ አፈፃፀምን በሚመለከት፡- ፍትህን ለዜጎች ተደራሽ ከማድረግ አንፃር ፍርድ ቤቶች በተለያየ መንገድ ማለትም በተዘዋዋሪ ችሎት፣በምድብ ችሎት፣ በህግ የፍርድ ቤቶችን የሥረ-ነገር ሥልጣን ወደ ሥር ፍርድ ቤቶች በማዉረድ ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ወረዳ እና ከወረዳ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ወደ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች የሥረ- ነገር ሥልጣን በማዉረድ እንዲሁም ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለዜጎች የዳኝነት አገልግልቱን በአቅራቢያቸዉ ሆነዉ እንዲያገኙ ተደራሽ በማድረግ ሰፊ ሥራ ተሰርቷል፡፡ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዋናዉ ማዕክል፣ በምድብ ችሎትና በአራት ተዘዋዋሪ ችሎት ማዕከላት ጉዳዮችን በቀጥታ፣ በይግባኝና በሰበር ተቀብሎ ዳኝነት የሚሰጥ ሲሆን በ9ወር ከሚቀርቡ መዝገቦች ዉስጥ 92 ፐርሰንት ላይ ዉሳኔ ለመስጠት የታቀደ ሲሆን በማሻ ማዕከል 3 ዙር፣ በቦንጋ ማዕከል 5 ዙር፣ በቱም ማዕከል 3 ዙር በአሜያ ማዕከል 3 ዙር፣ በተዘዋዋሪ ችሎት የዳኝነት አገልግልት የተሰጠ ሲሆን በ9ወር ዉስጥ በሁሉም ተዘዋዋሪ ችሎት ማዕከላት 588 መዝገቦች ቀርበዉ 484 መዝገቦች ሲወሰኑ 104 መዝገቦች ወደ ቀጣዩ ሩብ ዓመት ተላልፈዋል፡፡ በመሆኑም አፈጻጸሙ 82.31 ፐርሰንት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡በአጠቃሊይ በሁለም ደረጃ ባለ ፍርድ ቤቶች በተዘዋዋሪ ችሎት ሥራ በ9 ወር 5383 መዝገቦች ቀርበዉ በ 4605 መዝገቦች ሊይ ዉሳኔ የተሰጠ ስሆን አፈጻጸሙም 85.54 ፐርሰንት መሆኑን ለመረዳት ተችሎሌ፡፡

መ/ኮ፣ የሸሪዓ ፍ/ቤቶች አፈፃፀም  ያለበትን ደረጃ  ቢገልጹልኝ ?
አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም፡- የሸሪዓ ፍ/ቤቶች አፈፃፀም በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ጠቅላይ ሸሪዓ እና በሥሩ ባለ የከፍተኛ እና ወረዳ ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የተከናወኑ ሥራዎችን በሚመለከት በክልሉ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ኒካህ ማሰርና ማስረጃ መስጠት ካለፈው ሩብ ዓመት የተሻገረ ባይኖርም አዲስ የቀረበ 23 መዝገቦች ሲሆኑ 23 መዝገቦች ላይ እልባት ተሰጥቷል፡፡ የቤተሰባዊ ችግሮችን ማስታረቅ የምክር አገልግልት መስጠት እና የይግባኝ መዝገብ መመርመር ካለፈው ሩብ ዓመት የተሻገረ የለም አዲስ የቀረበ 14 መዝገብ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡
መ/ኮ፣ ሌሎች የዳኝነት አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር የተሰሩ ስራዎችን ቢገልጹልን?
አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም፡-  የዳኝነት አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆን የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች አዋጅ  የሥረ-ነገር ሥልጣን ተጨምሮ እንዲወጣ በማድረግ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶችን በአዲስ መልክ በማደራጀትና በአዋጁ ላይ የግንዛቤ ሥልጠና በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገባ የማድረግ ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት በ9 ወር ዉስጥ በ860 በላይ ቀበሌዎች ላይ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶችን በማደራጀት ለ2781 ማህበራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች እና 679 ሬጂስትራሮች በአዋጁ ላይ ሥልጠና በመስጠት ወደ ሥራ እንድገቡ ተደርጓል፡፡


በዚህ መሰረት በ9ወር ዉስጥ በማህበራዊ ፍርድ ቤቶች የታዩ የዳኝነት አገልግሎትን በሚመለከት 4894 መዝገብ ቀርቦ 3727 መዝገብ ላይ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ 1167 መዝገብ ወደ ቀጣዩ ሩብ ዓመት መተላለፍ ችሏል፡፡
በመሆኑም ማህራዊ ፍርድ ቤቶች አዋጅ የጸደቀዉ ሐምሌ ወር 2016 ስሆን ዳኞችንና ሬጅስትራሮችን በአዲስ መልክ መልምሎና አሰልጥኖ ወደ ሥራ ማስገባት የተወሰነ ጊዜ የጠየቀ ቢሆንም በ9 ወር የተገኙ መልካም አፈፃፀሞችን በማስቀጠልና በድክመት /በጉድለት/ የታዩትን አፈጻጸሞችን በማሻሻል በዓመቱ ማጠቃለያ ላቅ ያለ ውጤት እንደሚመዘገብ ታሳቢ ተደርጎ እየተሰራ ይገኛል ፡
ከዚህ በተጨማሪ የዳኝነት አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የባህል ፍርድ ቤቶች አዋጅ በከልሉ ምክር ቤት ከጸደቀ በኋላ በ252  ማዕከላት የባህል ፍርድ ቤት  አስታረቅ ሽማግሌ ዳኞች እንድመለመሉና ሥልጠና እንድሰጣቸዉ ተደርጎ ወደ ሥራ እንዲገቡ በመደረጉ ማህበረሰቡ ጉዳዩነ ባለበት አከባቢ ላይ ሆኖ በሠላም መፍታት እንድችሉ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በመሆኑመም አምና በተመሳሳይ ወቅት ወደ ፍርድ ቤቶች ይቀርቡ ከነበሩ ጉዳዮች በ2017 በ9 ወሩ ከ9180 በላይ የፍትሐብሔር መዝገቦች ከመደበኛዉ ፍርድ ቤቶች መቀነሱን ያሳያል፡፡ ይህም በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ላይ ያለዉ ጫና መቀነሱንና  ተገልጋዩ ማህበረሰብ  በአቅራቢያዉ አከባቢ ዳኝነት በማግኘት ከወጪበማዳን የልማት ሥራዉ ላይ እንዲሆን እንዳስቻለ ያመላክታል፡፡
ፍርድ ቤቶች በቴክኖሎጂ ተደራሽ ከመሆን አንጻር ብዙ ሀብትና ክህሎት የሚጠይቅ በመሆኑ ገና ብዙ የሚቀረን ቢሆንም የተጀማመሩ እና እየተሞከሩ ያሉ ሥራዎችን አጠናክረን በመሥራት በቴክኖሎጂ ተደራሽነት ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት እንደም ጠበቅብን ነዉ፡፡
መረጃ ለመስጠትና ከጠቅላይ ፍርድ ቤት መረጃ ለመቀበል  ለሚፈልጉ ተገልጋዮችና ማህበረሰብ ክፍሎች 8943 አጭር ጥሪ ማዕከል  ያደራጀን  በመሆኑ  በመደወል መረጃ መስጠትና መቀበል እንደምትችሉ በዚህ አጋጣም እያስታወኩ ፤ በአጠቃላይ የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት ለማሻሻል በፍርድ ቤት በዳኞችና ሠራተኞች ብቻ የሚፈጸም ባለመሆኑ መላዉ ህዝብና ባድርሻ አካላት በአከባቢዉና በየደረጃዉ ባሉ ፍርድ ቤቶች  በሚሰጡ የዳኝነት አገልገሎቶች ላይ በሚታዩ ጉድለቶች ላይ ተሳትፎ በማድረግ መረጃ በመስጠት  ጉድለቶች እንድታረሙ  የበኩላቸዉን ድርሻ እንድወጡ  ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
መ/ኮ፡- ለሰጡኝ ማብራሪያ ከልብ አመሰግናለሁ ፡፡
አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም ፡- እኔም አመሰግናለሁ ፡፡

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *