




”ዓላማ ተኮር ተግባቦት፣ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሁሉም አከባቢ ከተወጣጡ የኮሙዩኒኬሽንና የሚዲያ ባለሙያዎች እና የኪነ-ጥበብ ሙያተኞች ጋር የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የኮሙዩኒኬሽንና የሚዲያ እና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ከውይይት መድረኩ ጎን ለጎን በክልሉ ቦቦንጋ ከተማ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ እየተገነባ ያለውን የመደመር ትውልድ ቤተ መጻሕፍት እና በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ቅርብ ክትትል የተገነባዉን የቦንጋ ከተማ ኮሪደር ልማት አካል የሆነዉን የአረንጓዴ ፓርክ ጉብኝት አድርገዋል።
ከጉብኝቱ ተሳታፊዎች መካከል ከሸካ ዞን የመጡት አቶ ዋስሁን ዋጋኖ መንግስት ለጥበብ ትኩረት ሰጥቶ ለሀገር ግንባታ ለመጠቀም ስራ መጀመሩ እንዳስደሰታቸው እና በከተማው የተጀመሩ የልማት እንቅስቃሴዎች የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ የሚመልስ ስለሆነ ወደሌሎች አካባቢዎችም ተሞክሮዎችን ማስፋፋት ይገባል ብለዋል።
የኮንታ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ጎበና እንደገለጹት፤ ክልሉ የለውጡ ትሩፋት እንደመሆኑ መጠን ከለውጡ ወዲህ በክልላችን እየተከናወኑ ያሉ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች እጅግ በጣም ተስፋ ሲጪና ሊበረታቱ የሚገቡ ናቸው
ብዝሃ ከተሞች መካከል አንዷ በሆነችው ቦንጋ ከተማ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ እየተገነባ ያለውን የመደመር ትውልድ ቤተ መጻሕፍት በቀጣይ በዚሁ አካባቢ የተማረና አቅም ያለው
ትውልድ ከመፍጠር ረገድ ሚናው የጎላ በመሆኑ ይህንን የመደመር ትውልድ ቤተ መጻሕፍት ከማስተዋወቅ አኳያ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ተናግሯል፡፡
በመስተዳድር ዶክተር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ቅርብ ክትትል የተገነባዉ የኮሪደር ልማት አካል የሆነዉ የአረንጓዴ ፓርክ ብልጽግና ፓርቲ በከተሞች ለነዋሪዎች ሚቹ ለማድረግ ትልቅሚና እየተጨዋተ ያለ ፓርቲ ስለመሆ ማሣያ በመሆኑና በተለይም የቦንጋ ከተማ የቀድሞው ገጽታ በእጅጉ የቀየረ ነው ብለዋል።
ከምዕራብ ኦሞ ዞን የመጣው የኪነጥበብ ሙያተኛ ወጣት አንድነት ቶይዴ የመደመር ትውልድ ቤተ መፅሐፍ ግንባታ መንግስት በትውልድ ግንባታ ላይ እያከናወነ ከሚገኝ ተግባራት አንዱ እንደሆነ በመግለፅ ለሀገር ገፅታ ግንባታና አንድነት የራሱን አስተዋጽኦ ለማበርከት መዘጋጀቱን ገልጿል።
የአረንጓዴ ፓርክ አካባቢ ከዚህ በፊት እንደዚህ ያልነበረ መሆኑን አንስተው አሁን ግን በተሰራው ስራ ለመዝናናት፣ ለማንበብም ይሁን ቁጭ ብሎ ለማሰብ እጅግ ማራኪ ሆኖ አይተናል ነው ያሉት፡፡
በቦንጋ ከተማ የተጀመሩ የልማት ተግባራት ወደሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ማስፋት እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
ከዳውሮ ዞን የመጡት ወይዘሮ አዲስ ዘለቀ በሰጡት አስተያየት መንግስት የማህበረሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ኘሮጄክቶችን መጀመረ ብቻም ሳይሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ እያጠናቀቀ እንደሚገኝ በጉብኝቱ መታዘባቸውን ተናግረዋል።
በተለይ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የመደመር መፅሐፍ ሽያጭ እየተገነባ የሚገኘው የመደመር ቤተመጻሕፍት ግንባታ የመንግስትን የሀገር እና ትውልድ ቀረጻ ላይ አርቆ አሳቢነትን ገልፀው በኪነጥበብ ዘርፍ ለልማት እና መልካም አስተዳደር ዘርፍ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ሌላኛው የጉብኝቱ ተሳታፊ ከምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ዘውዴ፣ በቦንጋ ከተማ የተገነቡ ሁለቱ የልማት ፕሮጀክቶች ለከተማዋ የሚመጥኑ እና እጅግ ደስ የሚል መሆኑን አንስተው በቀጣይ ከዚህ የሚበልጥ ነገሮች እንደሚሰሩ ሙሉ እምነት እንዳለው ተናግሯል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤልና በካሳሁን አሰፋ
