




የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ለ114 የገቢ ተቋም ባለሙያዎች በሲግታክስ የመረጃ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ እየተሠጠ ነው።
የገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንዱ ታደሰ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው ቢሮው የታክስ አስተዳደርና የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን የዘመነ ለማድግ ከዚህ ቀደም ብዙ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።
ባለፋት ጊዜያት በሲግታክስ ተጠቅመን የግብር ግመታንና ውሳኔውን ለማውጣት የሚያስችል ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ጋር በመቀናጀት ስራ እየተሰራ እንደነበረ ያስረዱት አቶ ወንዱ በ2018 በጀት ዓመት በሁሉም የክልሉ ታክስ ማዕከላት የማንዋል አሰራርን በማስቀረት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ በሲስተም የታገዘ እንዲሆን የማድረግ ስራ ለመስራት ይህ ስልጠና ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በክልሉ 34 የታክስ ማዕከላት በሲግታክስ የመረጃ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ወስደው ወደ ተግባር መግባታቸውን የስታወሱት አቶ ወንዱ ታደሰ
ከዚህ በተጨማሪም በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ መንግስት የሲስተም ዝርጋታ በጀት ድጋፍ ለደተረገላቸው ለ31የታክስ ማዕከላት እንዲሁም በቀጣይ ቁሳቁስ ለሚሟላላቸው 4የታክስ ማዕከላት ስር ለሚገኙ የአወሳሰን፣ የአሰባሰብ እና የዕለት ገቢ ሰብሳቢ /ካሸር/ በሲግታክስ የመረጃ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ለ5ተከታታይ ቀናት ስልጠናው ይሰጣል ብለዋል።
ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በታክስ አስተዳደር ስርዓቱ መዘርጋቱ ግብር ከፋዩን በመመላለስ የሚያጠፋውን ጊዜና እንግልት የሚያስቀር ፍትሃዊና ቀልጣፋ የሆነ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት የምንገነባበት በመሆኑ ስልጠናውን በተለየ ትጋት መከታተል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
ከ6ቱ ዞን ለተውጣጡ 114 ባለሙያዎች የሚሰጠው ስልጠና የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን በማቀላጠፍ፣ የባለሙያ ስህተትን በማስቀረት፣ የስራውን ውጤታማነትና ተደራሽነትን በማሳደግ ረገድ አይነተኛ ሚና እንዳለው አቶ ወንዱ ተናግረዋል።
ከዚህ ስልጠና በኋላ ወደ ሙሉ ትግበራ ሲገባ የክልሉ ቴክኖሎጂ ተደራሽነት 98% የሚደርስ ይሆናል ያሉት ምክትል ኃላፊው ከክልል ባለ በጀት መስሪያቤቶች ተጨማሪ ቴክኖሎጂ መጠቀም የሚችሉ ግብር ከፋዮች ኢ-ታክስ፣ ኢ-ፋይልና ኢ-ፔይሜንት በመጠቀም ከሰዉ ንኪኪ ዉጪ ግብራቸዉን የሚከፍሉ ይሆናል ብለው በ2018 የግብር አሰባሰብ ስርዓቱ በሁሉም የታክስ ማዕከላት በሲስተም እንደሚከናወን ገልፀዋል፡፡
