መንግስት ለዜጎች ምቹና ተስማሚ አካባቢ ለመፍጠር እና የዜጎችን ህይወት ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል:-ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቦንጋ ከተማ “ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድረግ ” በሚል መሪ ቃል ክልል አቀፍ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ እየተካሄደ ነው ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንዳሉት፣መንግስት ለዜጎች ምቹና ተስማሚ አካባቢ ለመፍጠር እና የዜጎችን ህይወት ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ክልሉ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና እንክብካቤ እንደሚታወቅ ጠቅሰው አሁን በ”ጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄው ሁሉም የአካባቢውን ፅዳት ከመጠበቅ ባለፈ የአረንጓዴ ልማት ላይም የሚጠበቅበትን ድርሻ እንዲወጣ ያስችላል ብለዋል።

በገጠር የቤት እንስሳት ማደሪያ ቦታ ማዘጋጀት፣የሰዎች መኖሪያ ቤት ተከታትሎ ማስዋብና የሚመጥን ድዳት እንዲኖር ማድረግ፣በከተማና በመስሪያ ቤቶች ንጹህ የስራና የማረፊያ አካባቢ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚጠበቅ ጠቅሰው የንቅናቄ ስራው ውጤታማ እንዲሆን አሳስበዋል።

የኢፌዲሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሚ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር፣ጽዱና ተስማሚ ሀገርን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚስችሉ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው ይህ ክልል በአካባቢ ጥበቃ ጥሩ ምሳሌ ያለው እንደሆነም ጠቅሰዋል ።

የአካባቢያችን ለዜጎች ምቹና አረንጓዴ ለማድረግ እየተሰራ ያለዉ ስራ ከዚህን በፊት ከነበረው በተሻለ መልኩ እንደሆነ ገልጸዋል።

ዛሬ የተጀመረው “ጹዱ ኢትዮጵያ” ውጤታማ እንዲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል ።

በመድረኩ የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ሰነድ በክልሉ ደን አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለዉጥ ቢሮ ኃላፊ በሆኑት ዶ/ር ኢንጂነርሸአስራት ገ/ማርያምና የከተሞች ጽዳትና ዉበት ማስፈጸሚያ ደንብ በክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ በሆኑት በኢንጂነር የማታለም ቸኮል እየቀረበ ይገኛል።

በካሳሁን አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *