የሥርዓት፣ የባሕልና የኢኮኖሚ ድቀት ከዓለም ጋር እንድንተላለፍ አድርጓል – ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

የሥርዓት፣ የባሕልና የኢኮኖሚ ድቀት ከዓለም ጋር እንድንተላለፍ አድርጓል – ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ የገጠማት የሥርዓት፣ የባሕል እና የኢኮኖሚ ድቀት ከዓለም ጋር እንድትተላለፍ አድርጓል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መንግስት በተሰኘው አዲሱ መጽሐፋቸው ዙሪያ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ ሌላው ዓለም ፈጥኖ እኛ ወደ ኋላ የቀረንበት ዋነኛው ምክንያት ከሌላው ዓለም ባነሰ ፍጥነት በመጓዛችን ነው ብለዋል።

በድምሩ ሲታይ ሀገራዊ አቅሞች ሲዳከሙ የሚያጋጥም ውስንነት እንደሆነ አንስተው÷ ይሄንን ሃሳብ የመደመር መንግስት መጽሐፍ በዝርዝር ማስቀመጡን ተናግረዋል።

ሀገራዊ አቅሞች እንዲዳከሙ እና ከዓለም ጋር እንድንተላለፍ ያደረገው አንደኛው፣ የሥርዓት እና የተቋማት መበስበስ፣ መዳከም እና ቀጣይነት አለመኖር እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ይህም ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በተገቢው መንገድ እንዳይወጡ እንደሚያደርጋቸው ነው የተናገሩት፡፡

ከባሕል መበስበስ ጋር ተያይዞም አሁን ላይ እንደሚታየው ስራ የማይሰሩ እና የማያሰሩ፣ የሚሳደቡ፣ ዕውቀት የሚጠሉ፣ ማድነቅ የሚተናነቃቸው እንዲሁም ለመደማመጥ ቦታ የሌላቸው ሰዎች እየተበራከቱ እንዲመጡ ማድረጉንና ይህም ያለንን መተማመን እንዲዳከም ማድረጉን አስረድተዋል፡፡

የኢኮኖሚ ድቀትና መበስበስን በተመለከተም በፍላጎት እና በአቅርቦት መካከል ያለው ክፍተት እየሰፋ እንዲሄድ እንደሚያደርግ ጠቁመው÷ሰዎች በችግር ውስጥ ሆነው የነበራቸውን የመከባበር ባህል እንዲያጡ ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል።

እነዚህ ሦስቱ ድቀቶች ወይንም መበስበሶች እርስ በርሳቸው ተያያዥ እንደሆኑና የሦስቱ ዑደት ኢትዮጵያ አብራ ከነበረችባቸው ሀገራት ወደ ኋላ እንድትቀር ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

መጽሐፉ እነዚህን የሦስቱ ዋና ዋና መሰረቶች የመበስበስ ችግርን በዝርዝር ከተመለከተ በኋላ መውጫ መንገዱን እንደሚያመላክት ነው ያብራሩት።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *