የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ውስጣዊ አንድነትና ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማጠናከር ይገባል

Spread the love

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ውስጣዊ አንድነትና ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማጠናከር ይገባል

የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ውስጣዊ አንድነትንና ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማጠናከር ይገባል አሉ።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት አስመልክቶ “መገናኛ ብዙሃን ለብሔራዊ ጥቅምና ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ አውደ ጥናት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ‘ሚዲያ ለብሔራዊ ጥቅም’ በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ሁሉም ዜጋ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሁለንተናዊ መንገድ ለማስከበር በአንድነት መረባረብ አለበት።

የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ ማንኛውንም እንቅስቃሴ በሀሳብ የበላይነት መሞገትና ማክሸፍም እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለዚህም ውስጣዊ አንድነትና ሰላምን በማስጠበቅ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማጠናከርና የዴሞክራሲ አቅም በመገንባት መረባረብ እንደሚገባ አብራርተዋል።

መንግስት የኢትዮጵያን ብልፅግና በሁለንተናዊ መንገድ ለማረጋገጥ በሁሉም መስክ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው፤ መገናኛ ብዙሀን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር ላይ አጀንዳ ፈጥረው መስራት አለባቸው ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *