የሸካቾ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል/ማሽቃሬ ባሮ/በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ

በዓሉን በደመቀና በተሳካ ሁኔታ ለማክበር የብሔረሰቡ ተወላጆች፣ ወዳጆች፣የዞኑ ህዝብና ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ሲል የሸካ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ጥሪ አቅርቧል።
የዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀመረ ተሰማ በሰጡት መግለጫ የሸካቾ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል/ማሽቃሬ ባሮ/በደማቅ ሁኔታ ለማክበር በቂ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በዓሉን በደመቀና በተሳካ ሁኔታ ለማክበር የብሔረሰቡ ተወላጆች ፣ ወዳጆች፣የዞኑ ህዝብና ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ሲል ጥሪ አቅርበዋል።
በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ከዞን፣ከወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ እንዲሁም በየደረጃው ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ተግባር የተገባ መሆኑን ገልፀዋል አቶ ጀመረ።
የሸካቾ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል/ማሽቃሬ ባሮ/ የአንድነት፣የአብሮነት፣የሠላምና የፍቅር መገለጫ መሆኑን ገልፀው በዓሉ መስከረም 20/2018 ዓ.ም በሸካቾ ንጉስ መናገሻ አንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርም መምሪያ ኃላፊው በመግለጫቸው ማመልከታቸዉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
