ኢትዮጵያ ወደ ምግብ ሉዓላዊነት ከፍታ

Spread the love

ኢትዮጵያ ወደ ምግብ ሉዓላዊነት ከፍታ

መንግስት ለ2017/18 ምርት ዘመን ብቻ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ 84 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል፡፡ የማዳበሪያ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል፡፡ የዘንድሮዉን እንደ አብነት ካነሳን ከአምናዉ ፍላጎት ጋር ሲነጻጸር የ4 ሚሊዮን ኩንታል ብልጫ አለዉ፡፡

እንደ ሀገር ለማዳበሪያ ግዥ ከምናወጣዉ ወጪ በተጨማሪ ለትራንስፖርት አገልግሎት የምንከፍለዉ ዋጋ የዉጭ ምንዛሬ አቅማችንን ለዘመናት እያሟጠጠ በሀገር ኢኮኖሚ ላይም አሉታዊ ጫና እየፈጠረ ይገኛል፡፡

የለዉጡ መንግስት የአርሶ አደሮችን የዘመናት ጥያቄ ለመመለስና በየጊዜዉ ለማዳበሪያ ግዥ የሚወጣዉንም የዉጭ ምንዛሬ ለማስቀረት በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኝ በአጭር ጊዜ የተመዘገቡ ስኬቶች ማሳያ ናቸው፡፡

የብልጽግና ፓርቲ በኢኮኖሚ ፕሮግራሙ የሕዝባችን ሰፊ ክፍል የሆነውን አርሶ አደር፣ አርብቶ አደር፣ ወጣት፣ ሴቶች እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የከተማ ነዋሪዎች ማዕከል ያደረገ አካታች የኢኮኖሚ ሥርዓት በመገንባት የሕዝባችንን የጋራ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ዓላማ አንግቦ እያሳካ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ከወራት በፊት ሰኔ 26/2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በቅርቡ እንጀምራለን ብለዉ የገቡትን ቃል ከአንድ ወር በኋላ ወደ ተግባር አስገብተዋል፡፡ ስምምነቱ የፕሮጅክቱን መጀመር ምዕራፍ አብስሯል፡፡ ይህ ብስራት ለግብርና ዘርፍ ብቻ እምርታ የሚያመጣ አይደለም፡፡ በተግባር የሚገለጥ ሁለተኛ ሀገራዊ ህዳሴም ነዉ እንጂ፡፡

ኢትዮጵያን ማዳበሪያ ከመግዛት እክስፖርት ወደ ማድረግ ያሸጋግራታል፡፡ በአፍሪካ አህጉር የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት ያጠናክራል፡፡ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን በመቻል የዳቦ ጥያቄዋን እንድትመልስ ያደርጋታል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል በተደረሰው ስምምነት የሚገነባው የማዳበሪያ ማምረቻ ፋብሪካ ከውጭ የሚገዛን ማዳበሪያ በማስቀረት ብዙ ቢሊዮን ዶላር ወጪን ይታደጋል፡፡

ፋብሪካው ከማዳበሪያ ማምረት በተጨማሪም የተፈጥሮ ጋዝን በማልማት በግብርና፣ በማዕድን እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ትልቅ ሚና ይኖረዋል፡፡ ይህ የማዳበሪያ ፋብሪካ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት በማፋጠን ረገድ ሚናው የጎላ ሲሆን ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድልን ለመፍጠር እና ልማትን ለማነቃቃት ያግዛል፡፡

ፕሮጀክቱ አርሶ አደሮቻችንን በማጎልበት የግብርናዉን ዘርፍ በማሸጋገር የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት መሰረት የሚያረጋግጥ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ በጥገኝነት ሳይሆን በምርታማነት፤ በጽናት እና በሉዓላዊነት እንደሚሆን ፕሮጀክቱ ይመሰክራል፡፡

ሜጋ ፕሮጀክቱ ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በላይ ትርጉም አለዉ፡፡

ኢትዮጵያ ካለፉት ዉስንነቶች ተሻግራ የወደፊቱን የተትረፈረፈ እድል ለመቀበል ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ምልክት ነዉ፡፡

ኢትዮጵያ ከተስፋ ወደሚጨበጥ ብርሃን እየተሸጋገረች ነዉ፡፡ የብልፅግና ራዕዮች በተግባር እየተገለጡ የኢትዮጵያን ነገ ብሩህ የሚያደርጉ ዉጤቶችን እየተመዘገቡ ይገኛሉ፡፡ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግን ጥቅል አላማዉ ያደረገዉ የብልጽግና ፓርቲ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና የማኅበራዊ ብልጽግናን በሁለንተናዊ መልኩ እዉን ለማድረግ ያነገበዉን አላማ እያሳካ ይገኛል።

በኢኮኖሚ ዘርፍ በተለይም በግብርና ላይ የተመዘገቡ እምርታዊ ዉጤቶች የታሪክ እጥፋት ያመጡ ናቸዉ፡፡ በስንዴ ምርት እንደ ሀገር አንገታችንን ቀና ያደረግንት ስኬት የተመዘገበዉ በፓርቲዉ የአመራር ቁርጠኝነት ነዉ፡፡ በማህበራዊም ይሁን በፖለቲካ መስክ የተመዘገቡ ስኬቶች በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ነገ ላይ የተስፋ ብርሃን የፈነጠቁ የብልፅግና መሰረት የሚያፀኑ ናቸዉ፡፡

#prosperity

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *