ክልሉ ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተጠቆመ።

Spread the love

ከጅማ ታርጫ 800 መቶ ያስከፈለዉ አሽከርካሪ 5,000 ሺህ ብር ተቀጥቷል።

አሽከርካሪዉ ከሌሊት 7:00 ሰዓት ተሳፋሪን በህገ ወጥ መንገድ ይዞ መንቀሳቀሱም ተገልጿል።

መነሻዉን ጅማ መድረሻዉን ታርጫ ያደረገ ህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ ታርጋ 3_ኦሮ 65344 የሆነዉ ተሽከርካሪ ህጋዊ ታሪፍ 372 ብር ሆኖ እያለ ከአንድ መንገደኛ 800 ብር በማስከፈሉ በትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መያዙንና ቅጣት መቀበሉ ተገልጿል።

አሽከርካሪዉ ተቆጣጣሪዎች አይኖሩም በሚል ማምሻዉን ከጅማ እንደወጣ የገለፁት ተሳፋሪዎች መስከረም 13 ቀን 2018 ከሌሊቱ 7:00 ሠዓት አሳፍሮ ሲመጣ ከተሳፋሪዎች በተሰጠዉ ጥቆማ መሠረት በዳውሮ ዞን ታርጫ ዙሪያ ወረዳ በአባ ዳህ ቀበሌ ሲደርስ መያዙን አመልክተዋል።

በህገ ወጥ መንገድ የተቀበለዉን 9,880 እንዲመልስ ሲደረግ ከታርፍ በላይ በማስከፈልእና በሌሊትጉዞ በማድረግ በደንቡ 557/2016 መሠረት 5,000 ብር ተከሶ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ተደርጓል።

ከጅማ ቦንጋ፣ ከሚዛን ቦንጋ፣ ጅማ ታርጫና ሌሎች አከባቢዎች ቀን የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ህገወጦችን ላይ የጀመሩትን ቁጥጥር ጠበቅ በማድረጋቸዉ ህገወጥ አሽከርካሪዎች ጉዞአቸዉን ከቀን ወደ ምሽት እያደረጉ በመሆኑ በሁሉም አከባቢዎች የ24 ሰዓት የቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ እና ህብረተሰቡ የሌሊት ጉዞ እንዳይጓዝ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክቱን አስተላልፏል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *