

“ቆይታ ከእኛ ጋር” እንግዳችን ፕሮግራም
የክልሉ አደጋ ስጋት ኮሚሽን ኮሚሽነር ከሆኑት ዶክተር ለማ መሠለ (ዶ/ር) ጋር ተቋሙ ትኩረት አደርጎ በሚሰራባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፣ በክልሉ የተለዩ የአደጋ ስጋቶች፣ በክልሉ የአደጋ ስጋት የተለዩ አካባቢዎች፣ በክረምንት ወራት የተከሰተ የአደጋ መጠን፣ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም አቅም ከመቻልና ከማምረት ፣ የባድርሻ አካላት ቅንጅት እንዲሁም የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ያደረግነው ቆይታ እንደሚከተለው ቀርቧል!
መንግስት ኮሙኒኬሽን (መ/ኮ)፡ የቆይታ ከእኛ ጋር ፕሮግራም እንግዳ ለመሆን ፍቃደኛ ስለሆኑ ከልብ እናመሰግናለን።
ለማ መሠለ (ዶ/ር) ፣ እናንተም ስለጋበዛችሁኝ አመሰግናለሁ።
መ/ኮ፦የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ትኩረት አደርጎ የሚሰራባቸው ምን ምን ላይ ነው?
ለማ መሠለ (ዶ/ር)፦ የክልሉ አደጋ ስጋት ኮሚሽን በክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር አጠቃላይ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ ዘርፌ ብዙ ተግባራትን ያከናወናል።
ከነዚህም ዋና ዋናዎቹ መረጃን መሰብሰብ፣ አስቀድሞ ማስጠንቀቅ እና አደጋው ሲከሰት ጊዜ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም አደጋው ከተከሰተ ሂደቱን አጠቃላይ አደጋው ሊያመጣቸው የሚችሉ ጉዳዮችን መቀነስ ላይ በትኩረት ይሰራል።
በተጨማሪም በክልሉ የምግብ ዋስትና ስራዎችን በመምራት ችግር ባለባቸው አካባቢ ህብረተሰቡ ከችግር ተላቆ በምግብ ራሱን እንዲችል አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ላይ ይሰራል።
መ/ኮ፦ በክልሉ የተለዩ የአደጋ ስጋቶች ምን ምን ናቸው?
ክልሉ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት የሚታይበት እንደመሆኑ መጠን በክልሉ እንደ መሬት መንሸራተትና የጎርፍ መከሰት የአደጋ በዋናነት የተለዩ ስጋቶች ናቸው።
መ/ኮ፦ በክልሉ የአደጋ ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች በውል ተለይተው ይታወቃሉ?
ለማ መሠለ(ዶ/ር)፦በክረምንት ወቅት አብዘኛው ጊዜ ተጋላጭ የሚሆኑት የክልሉ ደጋማ አካባቢዎች ሲሆኑ በክልሉ ውስጥ እስከ ታችኛው መዋቅር በቅንጅት በተሰራው ስራ የተጋላጭነት ደረጃቸው የተለያየ ቢሆንም 37 ወረዳዎችንና በስሩ የሚገኙ 269 ቀበሌዎችን በመለየት መረጃን ቀድሞ የመስጠትና የማስጠንቀቅ ስራ ተሰርቷል።
የተጋላጭነት ደረጃው ከፍተኛ በሆነበት አካባቢዎች አደጋው ከተከሰተና ሰዎች ከተፈናቀሉ የሚጠለሉበትና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የመለየትና የአደጋ ዝግጁነት ስራ ተከናውኗል።
ያልታሰበና ቅጥበታዊ አደጋ የሚከሰት ከሆነ አስፈላጊውን ሰብአዊ ድጋፍ ለማከናወን ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ከዋናው መጠባበቂያ በማውጣት በሚዛን አማን፣ በቦንጋና ታርጫ ማዕከል እንዲሁም ምግብ ነክ ጉዳዮች በዋናው መጋዘን ዝግጁ ተደርጎ ይገኛል።
የአደጋ ምላሽ በዋናነት ከመንግስት የሚሰጥ ዕርዳታ ሳይሆን የቤተሰብ ባለቤትነትንና የማህበረሰብ አጋሪነትን በማረጋገጥ ሰብአዊ ድጋፍን በራስ እንዲችሉ ከማድረግ አንጻር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
ይህን ስራ ለማሳለጥ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት እስከ ቀበሌ በማቋቋም ግንዛቤን የመፍጠርና ድርሻውን የመከፋፈል ስራ በሰፊው ተከናውኗል።
መ/ኮ፦ በክልሉ ውስጥ የተከሰተው የአደጋ መጠን በውል ማወቅ ይቻላል?
በዚህ ክረምንት በክልሉ የከፋና ከአቅም በላይ የሆነ አደጋ ያልተከሰተ ቢሆንም በሁለት ወረዳ በ20 ቀበሌ በ260 አባወራዎች ላይ መጠነኛ አደጋ በማሳ የተከሰተውን የወረዳና በቀበሌ አቅም መቆጣጠር ተችሏል።
በ11 ወረዳዎች በ20 ቀበሌ በ80 ቤቶች ላይ የተከሰተውን መለስተኛ አደጋ ከዞን እስከ ወረዳ ባሉ መዋቅሮች ተከላክለዋል።
መ/ኮ፦ የአደጋ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች በዘላቂነት ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች፦
ለማ መሠለ (ዶ/ር)፦ ለአደጋው ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት በጥናት ላይ የተመሠረተ ከአካባቢው ወደ ሌላ አካባቢ የማስፈር ስራ በተለያዩ አካባቢዎች ከታችኛው መዋቅርና ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነው።
ለአብነት ከሰሜን ቤንች ወረዳ የተለዩ 89 ሰዎችን ወደ ጉራ ፋርዳ ወረዳ ወስዶ ለማስፈር ከዞኑ መንግስት ጋር በቅንጅት መሬት የመለየት ስራ እንዲሁም የቤት ግንባታ የሚሆኑ ግብዓቶችን በማቅረብ ላይ እንገኛለን።
ሳይታሰብ የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቆጣጠር እስከ ወረዳ በተፈጠረው የመጠባበቂያ ፌንድ ስርዓት ከ25 ሚለየን በላይ ብር እና ሌሎች ቀሳቁሶች አሉን ምግብ ነክ ያልሆኑ ግብዓቶችን ለማቅረብ ዝግጁ ናቸው።
መ/ኮ፦አደጋ ስጋትን ለመቀነስና ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ዕውን ለማድረግ በሚሰሩ ተግባራት የባለድርሻ አካላት ቅንጅምን ይመስላል ?
ለማ መሠለ(ዶ/ር)፦ ክልሉ የሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ዕውን ለማድረግ በአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤት አባል ተቋማትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በመናበብ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
መ/ኮ፦በዘላቂነት ምርታማነትን በመጨመር ከዕርዳታ ጥገኝነት ለማላቀቅ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ካሉ?
ከዕርዳታ ጥገኝነት በመውጣት አደጋዎችን ተቋቁመው ማለፍ የሚያስችል ክልላዊ ሁኔታ ለመፍጠር ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የማምረት ስራ ተጀምሯል።
በዚህም በበልግ እርሻ 383.75 በሄክታር ማሳ በወረዳዎች በዘር መሸፈኑንና ከዚህም 277.5 ኩንታል እህል በዞኖች መጋዘን ይገኛል።
በመኸር እርሻ 488.73 በሄክታር ማሳ በዘር ተሸፍኖ ይገኛል። በተጨማርም 406 ኩንታል እህል በክልል መጋዘን መጠባበቂያ ውስጥ ይገኛል።
የታችኛው መዋቅር የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ከማስቻል አንጻር በበልግ ወቅት በቆሎን በኩታ ገጠም ለሚያለሙ አርሶ አደሮች 500ሺ ብር የዘር ድጋፍ ተደርጓል።
መ/ኮ፦ በመጨረሻ የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ?
ለማ መሠለ (ዶ/ር)፦ አደጋ ጊዜና ቦታን የማይመርጥ፣ በተለይ በክረምንት ወቅት ተጋላጭነቱ የሚበዛ በመሆኑ በክልላችን የክረምት ወቅቱም እስከ ጥቅምት አጋማሽ የሚቀጥል በመሆኑ ቀድመው የተለዩ በተለይ የክልሉ ደጋማ አካባቢዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ፣ ድጋፍ እንዲሁም የሜትሮዎሎጂን መረጃ ቀድሞ በመውሰድ በንቃት መከታተል እንደሚገባ ጥሪውን አቀርበዋል ።
በጌታሁን ግርማ
