
የቱሪዝም ዘርፉን ወደ ጉልህ የእድገት አንቀሳቃሽ ሞተር መቀየር ተችሏል – ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
ባለፉት የለውጥ ዓመታት የቱሪዝም ዘርፉን ወደ ጉልህ የእድገት አንቀሳቃሽ ሞተር መቀየር ተችሏል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ፡፡
ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ ስብሰባ ዛሬ ተካሂዷል፡፡
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ መክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ መንግስት ባለፉት ዓመታት የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህም አዝጋሚ የነበረውን የቱሪዝም ዘርፍ ጉዞ ወደ ጉልህ የእድገት አንቀሳቃሽ ሞተር መቀየር መቻሉን ገልጸዋል።
በቀጣይም አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን የማስፋት፣ ነባሮቹን ደግሞ ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡
የቱሪዝም ዘርፉን የማስፋት ስራው የህዝቡን ወግ እና ባህል ባከበረ እና የህዝቡን ጥቅም ባረጋገጠ መልኩ እንደሚሆን አረጋግጠዋል፡፡
በተያዝው በጀት ዓመት የማህበረሰብ ቱሪዝም በመገንባት የመዳረሻ ስፍራዎችን ከአየር ትራንስፖርት ጋር የማስተሳሰር ስራ እንደሚከናወንም ተናግረዋል።
