




በሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም በዘላቂነት እንዲረጋገጥ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በየደረጃው የድርሻውን ሊወጣ እንዲችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል።
የመንግስት ሠራተኛው አስፈላጊውን እውቀት ጨብጦ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል።
የሀገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመወሰን፣ የበለፀገች ሀገር ለማስረከብ በየደረጃው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ፣ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ብልፅግና እውን እንዲሆን የበኩላችንን መወጣት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ኢኮኖሚያችን እየዳበረ ሲሄድ ተፅዕኖ የማሳደር አቅማችን እየጨመረ ስለሚሄድ ታሪካዊ አቅማችን ማሳየት እንደሚቻል ተገልጿል ።
ኢትዮጵያ አሁን የደረሰችበት የልማት ማንሰራራት ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ ፈተናዎችን የጋራ አረዳድ በመያዝ እልባት እየሰጡ መሄድ ይገባል ።
ብሄራዊ ጥቅም እና የጂኦስትራቴጂ ቁመና በሚል ሀሳብ የስልጠና ሰነድ እየቀረበ ይገኛል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
