



በምዕራብ ኦሞ ዞን “ብሄራዊ ጥቅሞችና ጂኦስትራቴጂክ ቁመና”
በሚል መሪ ቃል ለዞን አጠቃላይ መንግስት ሠራተኞች የስልጠና መድረክ ውይይት ተካሄደ ።
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩ የምዕራብ ኦሞ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በድሉ መዓዛ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞ ለማስጠበቅ እና ሀገራዊ ግብ እንዲሳካ የመንግሥት ሠራተኞች ላቅ ያለ ሚና መወጣት እንዳለበት ነው የተገለጸው ።
አቶ በድሉ አክለው እንደሀገር በርካታ አንጽባራቅ ስኬቶችንና ድሎች በመንግስትና በፓርቲ ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀው የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ውስጣዊ አንድነታችንን በተገቢው መረዳትና የሀገራችን ብሄራዊ ጥቅሞችና ጂኦስትራቴጂክ ቁመና መገንዘብ ይገባል ብለዋል።
የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አቤል ኢሳያስ እንደገለፁት የፓርቲያችንን እሳቤዎችና እሴቶች እንዱሁም ብሄራዊ ጥቅሞችና ጂኦስትራቴጂክ ቁመና ለአባላት በተገቢው መንገድ ማስገንዘብ ሀገራዊ ግብ እንዲሳካና የኢትዮጵያ የኩስማ ታርክ ማብቅያ ዘመን ላይ መሆናችንን
በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የህዝባችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፈተና ሲመጣ የማይናወጥ ቁመና ያለው የሀገራችን ባንዳዎችን ሀሳብ የሚመክት በየተሰማራበት መስክ በትጋት የማሠራ ስብልሰርቫንት መፍጠር ይገባል ሲሉ አቶ አቤል ገልጸዋል ።
በየተቋማቱ የሚታዩ ህዝቡን የሚያማርሩ ብልሹ አሰራሮች፣ የሚታዩ ህገ-ወጥ ንግድና የዋጋ ጭማሪዎች፣ የገበያ ቁጥጥር ማነስ እንዲሁም እየተሰሩ ያሉ መሰረተ ልማቶች ጥራት ላይ ክትትል እንዲደረጉና ለሚታዩ ችግሮችም አፋጣኝ መፍትሔ ሊበጅላቸው ይገባል ብለዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
