



በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የየዘርፉ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የአስፈፃሚ አካላት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች የአስፈጻሚ አካላትን ሪፖርት በሚገባ በመገምገም በጠንካራ ጎን የተገመገሙትን የማስቀጠል እና በድክመት የታዩት ላይ ገንቢ ግብረ መልስ በመስጠት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት መወጣት አለባቸው ብለዋል።
በመድረኩ የ5 የዘርፍ የአስፈፃሚ አካላት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል።
በካሳሁን አሰፋ
