ጠንካራ የተደራጀ ክትትልና ድጋፍ ለላቀ ድልና ስኬት የማይተካ ሚና እንዳለው ተገለፀ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስተት የድጋፍና ክትትል ቡድን በቤንች ሸኮ ዞን ተገኝተው ድጋፋ ማድረግ ጀምሯል።

የክልሉ ደን አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢንጂነር አስራት ገ/ማሪያም እንደተናገሩት የዚህ ድጋፋዊ ክትትል ዋና አላማ በዞኑ በእቅድ ተይዘዉ እየተከናወኑ ያለና መከናወን ያለባቸዉ የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎችን በተባበረ ክንድ እዉን ለማድረግ ተከታታይና ቋሚ የድጋፍና ክትትል ስርኣት በመዘርጋት ዞናዊ የአፈፃፀም ብቃትና ጥራት እንዲረጋገጥ ማስቻል እንደሆነም ተናግረዋል።

በክልል እና በዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴ የሚመራ የፖለቲካ አመራር ስብጥሩን በጠበቀ መልኩ የተደራጀ ድጋፋዊ ክትትል እስከታችኛው መዋቅር ድረስ እንደሚሰጥም ጠቅሰዋል።

አያይዘውም በዞኑ ባሉ ወረዳዎች ለተከታታይ ሶስት ወራት የሚቆይ ድጋፋዊ ክትትል በማድረግ በልማት፣ በመልካም አስተዳዳር፣ በሰላምና ፀጥታ እንዲሁም በፖለቲካ ስራ ላይ ድጋፍና ክትትሉ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በዚህም ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ የአገልግሎት እርካታና የህዝብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በየወሩ ድጋፋዊ ክትትል አፈፃፀም በዞን ደረጃ እየገመገሙ ምርጥ ልምዶች እየሰፉ እንዲሄዱ በማድረግ በመዋቅሮች መካከል የአፈፃፀም መቀራረብ እንዲፈጠር ለማድረግ እንደሆነም ተገልጿል።

የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር የማታለም ቸኮል የፖርቲና የመንግስት ኢኒሼቲቭ ስራዎች እንደ ቤንች ሸኮ ዞን ምን ይመስላል ሚሉትን በጥልቀት እንደሚያዩ ገልፀዉ ሁሉንም ተቋማት ያሉ ጉድለቶችንና ጥንካሬዎችን በመለየት ጉድለቶችን በመሙላት ጥንካሬዎችን በማስፋት ክልሉ ውስጥ ካሉ ዞኖች ፊት እንዲሆን በጋራ እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

በዞኑ በምንጠብቀው ልክ ያልተከናወኑ ተግባራት በፓርቲ መሪነት እንዴት እየተከናወኑ እንዳሉና የንቅናቄ አጀንዳዎች ላይ የተሰሩ ስራዎች ያሉበት ደረጀጃ በማየት እንደዞን ነባራዊ ሁኔታ የመንግስት እና የፓርቲ አመራር የጋራ ዕራይ ላይ ለማተኮር ድጋፍና ክትትሉ ወሳኝ ነው ያሉት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መብራቱ መርክኔ ናቸው።

በዘንድሮ አመት እንደ ዞን የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካትና እንድ ሀገርም በዚህ አመት ለማሳካት የተቀመጡ ትላልቅ ግቦችን በዞን ደረጃ እዉን ለማድረግ ከውትሮ በተለየ ሁኔታ የድጋፋዊ ክትትል ስርዓትን ዘርግቶ ወደስራ መገባቱን አንስተዋል።

አያይዘውም ከዞን እስከ ታችኛዉ መዋቅር በዉጤት የታጀበና የህዝብን እርካታ ያረጋገጠ ተግባርና አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ እስከ ጥር 30/2018 ዓም ድረስ የሚቆይና በክልሉና በዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴ እና በዞኑ አመራር የሚመራ የድጋፍ ቲም አደራጅቶ ለማሳማራት የሚያስችል የማስፈፀሚያ እቅድና ቼክ ሊስት መዘጋጀቱን አቶ መብራቱ ጠቁመዋል።

በድጋፍና ክትትሉ ወቅት የ2018 የመጀመሪያ ግማሽ አመት የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎች የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ማስፈጸሚያ እቅድና ቼክ ሊስት መሰረት ሪፖርት በዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ በአቶ ሽፈራው ቀርቧል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *