የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከል፦

Spread the love

👉🏾የሕዝብ እና የመንግሥትን የሰላም ጥሪን ባለመቀበል የሕዝብን ስቃይ እያበዙ ያሉ ኃይሎችን አደብ ለማስገዛት መንግሥት ምን ለመሥራት አስቧል?

👉🏾ትግራይ ክልል ወደ ሰላም ተመልሶ ልማት ውስጥ እንዲገባ ምን እየተሠራ ነው?

👉🏾የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ከማን ምን ይጠበቃል? በዚህ ረገድ የመንግሥት አቋምስ ምንድን ነው?

👉🏾የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ለሀገር ያላቸው አጠቃላይ ጠቀሜታ እና የመኖሪያ ቤት ግንባታን አስመልክቶ መንግሥት የያዘው ዕቅድ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጥ፣

👉🏾የአገልግሎት አሰጣጥን ለማፋጠን እና የፍትህ ሥርዓቱን ቀልጣፋ በማድረግ ረገድ ምን እየተሠራ ነው?

👉🏾 መንግሥት 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ መያዙን ይፋ አድርጓል። ይህን እቅድ ለማሳካት በመኖሪያ ቤት ግንባታ ላይ ምን እየተሰራ ይገኛል?

👉🏾የኑሮ ውድነቱትን አሁን ካለበት ለማሻሻል እና ሕገ-ወጦችን በዘላቂነት ለመቆጣጠር ምን እየተሰራ ነው?

👉🏾የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውጤታማነት እና የመጪው ጊዜ ተስፋ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጥ?

👉🏾በባሌ ዞን የተሰራው ድንቅ ሥራ የሚያስመሰግን ነው፤ ይህንን አጠናክሮ ለመቀጠል ምን እየተሰራ ነው?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *