ተገቢ የኤች.አይ. ቪ /ኤድስ ምርመራና የህክምና አገልግሎት በመስጠት የበሽታውን ስርጭት መቀነስ እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ አፈጻጸምና እና የ2018:ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ መከላከል (PMTCT)፣ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር(EXCA) እና የጉበት ቫይረስ (Hepatitis) ምርመራና ህክምና የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ በታርጫ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኃይሌ ዘውዴ ያለፈውን ጥንካሬ ማስቀጠልና የታዩ ጉድለቶች ለማረም የመድረኩ ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ 122,202 ነፍስ ጡር እናቶች የኤች. አይ.ቪ ምርመራ ከተለዩት መካከል 94,220 (77%) ከተመረመሩት ውስጥ 0.1% እናቶች ቫይረሱ በደማቸው መገኘቱን አንስተዋል።

በ2017 ዓ/ም የጉበት ቫይረስ (Hepatitis) ምርመራ አገልግሎት 122,202 ምርመራ ለማካሄድ ተይዞ 52,000 ተካሂዶ ከአፈጻም አንጻር 42% ላይ በመሆኑ 0.9% ፖዘቲቭ 514 እናቶች በመሆኑ ትኩረት ያስፈልጋል ብለዋል።

የማህፀን በር ካንሰር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩ፤ ብዙ እናቶች ተጋላጭነታቸው እየጨመረ መመምጣቱን ያስታወሱት አቶ ኃይሌ በ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸሙ በበሽታ መከላከል 21% ላይ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት እንደሚሻ ገልጸዋል።

ለዚሁ ተግባር በክልሉ 44 ተቋማት ስራውን ለማሳለጥ ስልጠና ወስዶ ግብዓት ተሟልቶላቸው ወደ ስራ ውስጥ መግባታቸውን በማንሳት በየተቋማቱ ያለው አፈጻጸም ወጥ ደረጃ ባለመሆኑ በዚህ በትኩረት እንዲሰራ አቶ ኃይሌ ተናግረዋል።

በ2017 ዓ/ም የወሊድ አገልግሎት ዝቅተኛ መሆኑን በማንሳት 1ኛ ሩብ ላይ 67% በመሆኑ ህፃናት ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ለመጋለጥ አስተዋጽኦ እንደሚበረክት በማንሳት እናቶች በጤና ተቋማት ከማዋለድ አንጻር ልዩ ትኩረት እንደሚፈልግ አሳስበዋል።

በመሆሆኑም ተገቢ ምርመራ፣ ጽዱ በሆኑ ተቋማት የማዋለድ አገልግሎት ማድረግ እንዲሁም የህክምና አገልግሎት እንዲጠናከር በአጽንኦት ተናግረዋል።

የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ኤች አይ ቭ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ከሰሪ የመድረኩ ዓላማው የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ መከላከል (PMTCT)፣ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር(EXCA) እና የጉበት ቫይረስ (Hepatitis) ምርመራና ህክምና አፈጻጸም ላይ በጋራ በመወያየት በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መሆኑን ገልጸዋል።

በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዘርፍ በትኩረት ከሚሰራባቸው አንዱ በሽታው ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ መከላከል (PMTCT) ፣ የጉበት ቫይረስ (Hepatitis እና የቅጥኝ በቅንጅት የሚሰሩ መሆናቸውን ጨምሮ ገልጸዋል።

በክልላችን እናቶች ቤት በመውለዳቸው፣ፀረ ኤች አይ ቪ ህክምና ዘገይቶ ከመጀመር፣ መድኃኒትን ተከታትሎ በጊዜ ከመውሰድ የጉበት ቫይረስ (Hepatitis አንጻር ክፍተት በመታነቱ እንደ ክልል ከእናቶች ወደ ልጅ የመተላለፍ ከፍ ብሎ ስለሚገኝ በትኩረት እንዲሰራ አቶ መንግስቱ አሳስበዋል።

በመሆኑም በመድረኩ ላይ ችግሮቹን በአግባቡ በመለየት በቀጣይ መፍትሔ መረባረብ እንደሚገባ በአጽንኦት ተናግረዋል።

የዞኖች የ2017 እና 2018 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት የPMTCT የአፈጻጸም ሪፖርት በየዞን መምሪያ ኃላፊዎች ለተሳታፊዎች እየቀረበ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኃይሌ ዘውዴ ጨምሮ የክልሉ ጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት፣ ዞን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊዎች።፣ የዞን መምሪያና የወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ሌሎች የባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *