ሙስናና ብልሹ አሰራርን የሚከላከል ማህበረሰብ በመፍጠር በተቋማት ደሞክራሲያዊ አሰራርን ማስፈን እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

‎”ትውልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር ” በሚል መሪ ቃል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት አዲስ ለተመደቡና ነባር የስነ ምግባር ዳይሬክቶረት ፣ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ እየተሰጠ ይገኛል።

‎በስልጠናው ማስጀመሪያ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ እንደገለፁት የሚሰጠው ስልጠና ሙስናና ብልሹ አሰራርን ከመከላከል ባለፈ ሰልጣኞችን አቅም የሚገነባና ልምድ ለመጋራት የሚያግዝ ነው ብለዋል።

‎የሙስና ወንጀልን መቀነስ የሚቻለው በስነ ምግባር የታነፀ ማህበረሰብ በመፍጠር መሆኑን ተረድቶ መቀራረብና መነጋገር እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።

‎ተቋማት ሙስናን የመከላከል ተግባር ላይ ትኩረት በማድረግ ለሚያገለግሉት ማህበረሰብ ታማኝ መሆን ይገባቸዋል ብለዋል።

‎ሙስናን ለመዋጋት በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መስራትን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ የትምህርት ተቋማት ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ለማፍራት መዘጋጀት እንዳለባቸው ገልፀዋል ።

‎ሙስና የፖለቲካ ወይም የኢኮኖሚ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር የሞራል ፈተና በመሆኑ የመከለል ትግሉ በቅንጅት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

‎መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ አሰራርን በተቋማት እንዲሰፍን በምክንያትና በውጤት የሚያምን ማህበረሰብ መፍጠር ስቻል በመሆኑ ተግባሮቻችን ከወትሮው በላቀ መልኩ ለማስኬድ ስልጠናው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለውም ገልፀዋል።

‎ቀጣይ በሚሰሩ የፀረ-ሙስና ትግል ስራዎች ሁሉ ተቋሙ ከኮሚሽኑ የህግ ከለላ እንዲያገኙም ይደረጋል ሲሉ ገልፀዋል።

‎ስልጠናው ሙስናን መከላከል በሚያስችሉ ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚሰጥ እንደሆነም ተመላክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *