ባለፉት ስድስት ወራት ጠንካራ ፓርቲ ግንባታን ለማፋጠን በርካታ ስራዎች መሰራታቸዉን አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ

Spread the love

ባለፉት ስድስት ተወራት ጠንካራ ፓርቲ ግንባታን ለማፋጠን በርካ ስራዎች ተሰርተዋል ሲሉ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ከዘርፉ አመራሮች ጋር እያካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንደ ፓርቲ የታለሙትንና ግቦችንና ተልዕኮዎችን በብቃት ለመፈጸም የተደረገው ሁለንተናዊ ጥረቶች አበረታች ውጤት ማስገኘቱን አንስተዋል።

በፓርቲያችን ሀሳብ አመንጭነት ተግባራዊ በተደረጉ ኢኒሼቲቮች በተለይ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ በሌማት ትሩፋት እንዲሁም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል።

በብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት የተቀመጡ ስድስቱ ግቦችን ለማሳካት መጠነ ሰፊ ርብርብ እየተደሰገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ከተረጂነትና ልመና በመላቀቅ የተሟላ ሀገራዊ ሉአላዊነትን ማረጋገጥ የታሪክ እጥፋት የሚያመጣ የፓርቲያችን ንቅናቄ ለማሳካት እየተደረገ ያለው ዘርፈ ብዙ ተግባራት በተጨባጭ ውጤት እያስመሰከረ ይገኛል ነው ያሉት።

የፓርቲና የመንግስት ድርብ ተልዕኮዎችን በውጤታማነት ለመፈጸም ከመቼውም ጊዜ በላይ ብርቱ ትግል ይጠይቃል ሲሉ አቶ ፍቅሬ አስገንዝበዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት በተግባር አፈጻጸም የታዩ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በማስቀጠል ክፍተቶችኝ ነቅሶ በመለየት ለቀጣይ የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ በስትራቴጂክ ስራ አመራር ዘርፍ ኃላፊ በሆኑት በአቶ አንተነህ አየለ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ እንደሚገኝ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *