የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ እየተደረገ ነዉ።

Spread the love

የክልሉ የአስፈጻሚ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ሴክተር መ/ቤቶች ግምገማ መድረክ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ሶስተኛ ቀኑን በያዘው የግምገማ መድረክ ላይ የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ ባስተላለፉት መልዕክት በ2018 በጀት ዓመት ሁለም ተቋማት በተናበበና በተቀናጀ ዕቅድ ወደ ተግባር እንዲገቡ መደረጉንና አፈፃፀሙንም ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል።

የተቋማት ዋና ዋና የልማት ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በሚስተዋሉ ክፍተቶች ላይ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የማስቀመጥ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነም ተናግረዋል።

ዛሬ ጠዋት በተያዘው መርሃ ግብር መሠረት የማህበራዊ ክላስተር ሴክተር መ/ቤቶች ከሆኑት ውስጥ የትምህርት ቢሮ፣የጤና ቢሮና ተጠሪ ተቋማት፣የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንዲሁም የባህል፣ተሪዝምና ስፖርት ቢሮ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሚቀርብ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የትምህርት ቢሮ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *