ለክልሉ ጂምናስቲክ ልዑካን ቡድን አቀባበል ተደረገለት::

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን በመወከል በኢትዮጵያ ጂምናስቲክ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ተሳትፈው ስምንት መዳልያዎችንና አንድ ዋንጫ በማግኘት ውድድሩን ያጠናቀቀው ልዑካን ቡድን ቦንጋ ከተማ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።

በአቀባበል መርሐግብሩ ላይ የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክት ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አህመዲን አወል፣ የክልሉ ጂምናስቲክ ፌደሬሽን ም/ፕሬዝዳንት አቶ አንተነህ አየለ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ ዲን እና የክልሉ ጂምናስቲክ ፌደሬሽን ም/ፕሬዝዳንት አቶ አንተነህ አየለ ለሉዕካን ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የልዑካን ቡድኑ ያገኘው ውጤት አበረቻችና ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልፀው በተወዳዳሪዎች ጥረት የተገኘውን ውጤት ይበልጥ ለማሻሻል በቀጣይ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ፌደሬሽኑ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አህመዲን አወል በበኩላቸው ከግላቸው ዝናና ጥቅም በላይ የክልሉ ስም ከፍ ብሎ እንዲጠራ ላደረጉት ለልዑካን ቡድኑ አባላት ምስጋና አቅርበው ለጂምናስቲክ ስፖርት ምቹ ሁኔታ ባልተፈጠረበት እንዲህ አይነት ውጤት ማምጣት መቻላቸው የሚያኮራ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ አህመዲን አክለው የጂምናስቲክ ስፖርትን በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በማስተዋወቅና ለስፖርቱ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር በቀጣይ ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረው ሁሉም የባለድርሻ አካላት ለስፖርቱ ዘርፍ ዕድገት የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ጥሪ አቅርበዋል።

በክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የተዘጋጀው የማበረታቻ የገንዘብ ስጦታ እንደየደረጃቸው ለልዑካን ቡድኑ አባላት የተበረከተ መሆኑንም አቶ አህመዲን ገልፀዋል።

የልዑካን ቡድኑ አንድ ዋንጫ፣ ሁለት የወርቅ፣ አንድ የብር እና አምስት የነሀስ ሜዳልያዎችን ማግኘቱ የሚታወስ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *