የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ስድስት ወራት 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎችን አጓጉዟል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ስድስት ወራት 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎችን ማጓጓዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በለውጡ ጅማሬ በዓመት ወደ 8 ሚሊዮን የሚጠጉ ደንበኞችን ያጓጉዝ እንደነበር አንስተው፤ አሁን ግን ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎችን አጓጉዟል ብለዋል።

የሞባይል ተጠቃሚ ዜጎች ቁጥርም በለውጡ ጅማሬ 37 ሚሊዮን እንደነበር ገልጸው፤ ይህ አሃዝ አሁን ላይ 97 ሚሊዮን መድረሱን አብራርተዋል።

የ5 ጂ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ከተሞች ቁጥርም በቅርቡ 30 የሚደርስ መሆኑን ተናግረዋል።

የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚ ዜጎች ቁጥርም 58 ሚሊዮን መድረሱን ገልጸው፤ ይህም የፖሊሲ ትኩረት ውጤት ነው ብለዋል ሲል አ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *