የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁስ ዝግጅት እየተከናወነ ነው- ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Spread the love

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚያስፈልጉ የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁሶችን የማደራጀትና የማሰራጨት ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።

ቦርዱ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን የማዘጋጀት ሥራዎችን ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች አስጎብኝቷል።

በዚሁ ወቅት በቦርዱ የሎጀስቲክስ ኃላፊ አቶ መላከ አሉላ፤ የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁሶችን ለየምርጫ ጣቢያዎቹ የመለየትና የመደልደል ሥራዎች በጥንቃቄ እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢቢሲ እንደዘገበው እነዚህ ቁሳቁሶች በአገር አቀፍ ደረጃ በ52 ሺህ 720 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሚሰራጩ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

ቁሳቁሶቹ ከመታሸጋቸውና ከመሰራጨታቸው በፊት በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በኩል ጥብቅ የጥራት ቁጥጥር እየተደረገባቸው መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ዝግጅት እየተደረገባቸው ከሚገኙ የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁሶች መካከል የመራጮች መመዝገቢያ ኪት፣ ስቴሽነሪዎች፣ የቅሬታ አፈታት መመሪያዎችና ፖስተሮች እንደሚገኙበት ኃላፊው አብራርተዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ አሁን ላይ የቁሳቁስ ማሸግ ሥራው በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ ሲሆን፣ ስርጭቱም በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለምርጫ ጣቢያዎች ተደራሽ እንደሚሆን ተመላክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *