ማዕከሉ ፈጣንና ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት በመስጠት ከዚህ ቀደም ይስተዋል የነበረ የህዝብ ቅሬታ መፍታት እያስቻለ ነው፦ የክልሉ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት

Spread the love

‎አገልግሎቱን ለማስፋት ታልሞ በተከናወነ ስራ በዞኖች አካባቢ የተጀመሩ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ተቋማት ግንባታ ሂደታቸው በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መሶብ አንድ ማዕከልአገልግሎት ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አህመዲን አወል እንደገለጹት በክልሉ የመጀመሪያ የሆነው የሚዛን-አማን ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለሕብረተሰቡ ሰፊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

‎በማዕከሉ አምስት የክልልና አራት የፌዴራል ተቋማት 35 የተለያዩ አገልግሎቶች እየተሰጡ እንዳሉ የገለጹት አቶ አህመዲን ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ወዲህ ከ24 ሺህ በላይ ዜጎች አገልግሎት መስጠቱን ተናግረዋል።

‎በክልሉ መሶብ አንድ ማዕከል ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ጊዜ ወዲህ 20 ሺህ 129 ተገልጋዮች ቀርበው ዲጂታል አገልግሎት ያገኙ ሲሆን 3 ሺህ 958 በላይ ተገልጋዮች ደግሞ መንቀሳቀስ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት ሆነው በኦንላይን መገልገል መቻላቸው ተገልጿል።

‎ማዕከሉ በተቀመጠ ስታንዳርድ መሠረት ከእጅ ንክኪ ነፃ ዲጂታል አገልግሎት እየሰጠ በመሆኑ ከዚህ ቀደም ይስተዋል የነበረ የህዝብ ቅሬታ መፍታት እያስቻለ መሆኑን አቶ አህመድን ተናግረዋል።

‎ማዕከሉ ለዜጎች በሚሰጠው አገልግሎት ከተገልጋዮች ኦንላየን በሰበሰበው የተገልጋይ እርካታ መሠረት 97 ነጥብ 6 በመቶ ለማድረስ የተቻለ ሲሆን በቀጣይ የተገልጋይ እርካታን መቶ በመቶ ለማረጋገጥ እየተሰራ እንዳለም አቶ አህመዲን ገልጸዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

‎መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመር በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ከሕብረተሰቡ ሲነሳ የነበረውን እንግልት፤ ጉልበትና የሀብት ብክነት በሰፊው እየቀረፈ እንደሚገኝ ምክትል ስራ አስፈፃሚው ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *