በዳውሮ ዞን ገና ወረዳ ከ49 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የፋንታ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

Spread the love

በዳውሮ ዞን ገና ወረዳ ባዛ ሾታ ቀበሌ በፓክት (PACT) – በተሳትፎአዊ ግብርናና አየር ንብረት ሽግግር ፕሮግራም አማካኝነት የሚገነባው የፋንታ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ በይፋ ተጀምሯል።

የፕሮጀክቱን መሠረተ ድንጋይ ያስቀመጡት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መሰተዳድና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ የፋንታ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት በክልላች የግብርናውን ዘርፍ እየተካሄደ ያለውን የብልጽግና ጉዞ የሚያፋጥን ነው ብለዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው የግብርናው ዘርፍ በአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተነደፉ ተልዕኮዎችን እና ግቦችን እውን ለማድረግ ህብረተሰቡንና የተለያዩ የልማት አጋሮችን በማስተባበር እየተጋ ይገኛል።

ከእነዚህ የልማት አጋሮች መካከል አንዱ የሆነውና ለዘርፉ ውጤታማነት አይነተኛ አስተዋጾኦ እያበረከተ የሚገኘው የተሳትፏዊ ግብርና እና የአየር ለውጥ ፕሮግራም አርሶ አደሩ በምግብ ሰብል ራሱን በዘላቂነት እንዲችል የሚያግዙ ድጋፎችን ተደራሽ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

ፕሮግራሙ በክልሉ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች ስር በሚገኙ 3 ወረዳዎች፤ በተመረጡ 5 ስነ ምህዳሮች ከ26 ሺህ 5 መቶ በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

አርሶ አደሩ በምግብ ሰብል ራስሱን ከመቻል ባለፈ በአካባቢው

ተኪ ምርቶችን አምርቶ ተጠቃሚ እንዲሆን በክልሉ ውጤታማ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝም አቶ ማስረሻ አመላክዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ውኃ ማዕድንና ኢነርጅ ቢሮ ኃላፊ ኢኒጂነር በየነ በላቸው በበኩላቸው ግብርናችንን ከባህላዊ አሠራር አውጥተን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የዚህ መሰል መሠረተ ልማቶች መገንባት ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።

ፕሮጀክቱን በተቀመጠለት ጥራትና ጊዜ አጠናቆ ለሕዝብ አገልግሎት ለማብቃት ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግም ኢኒጂነር በየነ አስገንዝበዋል።

የአካባቢው ማኅበረሰብም ለግንባታው መሳካት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ያቀረቡት የቢሮ ኃላፊው ይህ ልማት የሁላችንም ነው በሚል በባለቤትነት ስሜት ተረባርበን መገንባት አለብን ብለዋል።

የዳውሮ ዞን ዋና አርተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በበኩላቸው በዞኑ የሚገኙ የመልማት አቅሞች የብልጽግና ጉዟችንን እውን እንዲያደርጉ ተግባራዊ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል።

ዛሬ የመሠረተ ድንጋይ የተቀመጠለት የፋንታ አነስኛ መስኖ ፕሮጀክትም ለዚሁ ማሳያ ነው ያሉት ዋና አርተዳዳሪው ግንባታው ሲጠናቀቅ በአካባቢው የሚገኙ 241 አርሶ አደሮችን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል ሲሉም ገልጸዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ተሳትፎአዊ ግብርናና አየር ንብረት ሽግግር ፕሮግራም ሥራስኪያጅ አቶ ታመነ ተስፋዬ ፕሮጀክቱ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም የአካባቢውን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

ለፕሮጀክቱ ግንባታ 49 ሚሊዮን 546 ሺህ 332 ከ46 ሳንቲም መመደቡም ተመላክቷል።

በመሠረተ ድንጋይ ማስቀመጥ መርሃ ግብሩ ላይ በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የተመራ የክልል ፣ የዞን እና የወረዳ መንግስት አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *