




በዳውሮ ዞን ኢሳራ ወረዳ የተገነባውን የሰንገጢ -ጩርጩራ የመንገድ ፕሮጀክትተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
40 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው በዳውሮ ዞን ኢሳራ ወረዳ የተገነባውን የሰንገጢ ጩርጩራ መንገድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) መርቀው ከፍተዋል።
መንገዱ የተገነባው ከክልሉ መንግስት በተመደበው 83 ሚለየን ብር እና የዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ በተመደበው 35 ሚለየን ብር የካፒታል በጀት መሆኑን የክልሉ የመንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር አብዲዩ መኮንን ገልጸዋል።
በምርቃት መርሐ-ግብሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ የሆኑት አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ፣ ሌሎች የክልል፣ ዞንና ወረዳ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በጌታሁን ግርማ
