ለኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን የምናደርጋቸው ድጋፎች በሃገር ግንባታ ስራችን ላይ አሻራ የምንጥልበት በመሆኑ አስፈላጊውን የቅንጅት ሰራ በጋራ በመስራት ማገዝ ያለብንን የምናግዝ ይሆናል:-የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ::

Spread the love

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የአራት ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት በዳመጡበት ወቅት ለኮሚሽኑ የምናደርጋቸው ድጋፎች በሃገር ግንባታ ስራችን ላይ አሻራ የምንጥልበት በመሆኑ አስፈላጊውን የቅንጅት ስራ በጋራ በመስራት ማገዝ ያለብንን የምናግዝ ይሆናል ብለዋል።

የምክክር ኮሚሽኑ ሃላፊነትን በተላበሰ መልኩ ተልዕኮውን ለማሳካት የሚያገጥሙ ችግሮችን በመቋቋም የህዝባችንን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ የስራቸውን ሰራዎችን በጥንካሬ አንስተዋል።

በሃገር ደረጃ ያሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ከችግሩ መቅድም ያስፈልጋል ያሉት አፈ -ጉባኤው ለሃገራዊ ምክክሩ ሁሉም ተገዢ ሆነው እንዲሰሩ ከመንግስት መዋቅርና ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመመካከር እንዲሁም ሌሎች ድጋፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ተቋማት ጋር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በጋራ በመስራት ለሃገሪቱ ህዝብ የገባነውን ቃል መፈጸም ይኖርብናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በበኩላቸው በክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች በርካታ የቅድመ ዝግጅት እና የተሳታፊ ልየታ ስራዎች ማከናወናቸውን ገልጸው በክልል ደረጃ የሚደረጉ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ምክክር ሂደቶችን አስመልክቶ የአሰራር ስርአት በመዘረጋት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት በርካታ ስራዎችን ማከናወናቸውን አስረድተዋል።

በቀጣይም ከሚሽኑ የተሳታፊዎች ልየታ ባልተከናወነባቸው ክልሎች ልየታ በማድረግ አጀንዳዎችን በህዝባዊ ውይይቶች በማሰባሰብ ምክክሮች እንደሚካሄዱ ጠቁመው በዚህ ሂደት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያግዙ የባህል መሪዎችን የመለየትና ተቀራርቦ የመወያየት ስራዎችን እንሰራለን ብለዋል።

በሌላ በኩል በግጭቶች ምክንያት በክልሎች የተሳታፊዎች ልየታ ስራዎችን ለማጠናቀቅ መቸገራቸውን ያገጠራቸቸው ችግር እንደሆነ ሳይገልፁ አላለፉም።

በምክክር ሂደቱ ውጤታማ እና በሃገሪቱ የተሻለ የሰላምና የፖለቲካ መደላድል እንዲፈጠር ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅዖ ሊያበረከት ይገባል ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔዎች ጨምሮ የመንግስት ተጠሪዎች ፣ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና አባላት እንዲሁም የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ሚኒስትሮች እና ኮሚሽነሮች ሌሎችም የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች የኮሚሽኑን የአራት ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት አዳምጠዉ ሃሳብና አስተያየታቸውን መስጠታቸዉን ከምክር ቤቱ ማህበራዊ ትስስር ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *