


አዲሱ አርማ ዋና መምሪያው የተሰጠውን ተቋማዊ ግዳጅና ተልዕኮ በሚገልፅ መልኩ ተሰርቶ ርክክብ መደረጉ ተጠቅሷል።
በርክክብ ሰነ- ሰርዓቱ ላይ የተገኙት ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና ለተቋማዊ ዝማኔም ይሁን ለመምሪያው የግዳጅ አፈፃፀም ውጤት አዲስ የተሰራው አርማ /ሎጎ/ ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል።
መለያ ምልክቱን ለማሰራት ሰፊ ጥናት የተካሄደ መሆኑን የተናገሩት ጀኔራል መኮንኑ አርማው በጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዡር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፀድቆ ስራ ላይ እንዲውል መወሰኑንም ጠቁመዋል።
የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል አብነት ግርማ በበኩላቸው መለያ ምልክቱ የዋና መምሪያውን ተልዕኮና የግዳጅ ሁኔታ በግልፅ ማንፀባረቅ በሚችል መልኩ መሰራቱን ገልፀዋል።
ቀጣይ በሚከናወኑ የክፍሉ ሰራዎች ላይም ትልቅ አቅም እንደሚጨምር መናገራቸውን የመከላካያ ሰራዊት መረጃ ያመለክታል ያለው ኢዜአ ነው።
