ከ3 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የካፌቾ ብሔር የዘመን መለወጫን በጋራ ለማክበር በተደረገው ንቅናቄ ተሰብስቧል፦ የካፋ ዞን አስተዳደር

Spread the love

የዘንድሮውን የካፌቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በጋራ ለማክበር እየተደረገ ባለዉ የገቢ አሰባሰብ በእስካሁኑ ከ3 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የካፋ ዞን አስተዳደር ገለጸ

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በቀደምት አባቶች ገለዜ አንስቶ በየዓመቱ እየተከበረ ለብዙ ዘመናት የቆየውን የካፌቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነዉ ብለዋል።

በበዓሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የብሔሩ ተወላጆች እና የተለያዩ እንግዶች ይሳተፋሉ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደሥራ መግባታቸውን ጠቁመዋል።

በዓሉን ሁሉንም ህብረተሰብ በማሳተፍ በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች 21 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ይኼ መረጃ እስከተጠናቀረበት 3 ሚሊዮን 1 መቶ 44 ሺህ ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጸዋል።

በዚህም ከ5 መቶ በላይ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሁነዋል ብለዋል።

በገቢ ማሰባሰቡ ላይ ወጣቶች የግል ባለሀብቶች የመንግስት ሠራተኞች አመራሮች እና የተለያዩ አጋሮች እንደተሳፉም ጠቅሰዋል።

በቀጣይም በተለያዩ አጋጣሚዎች ያልተሳተፉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል።

በአጭር ግዜ ውስጥ በተጀመረው በዚሁ የገቢ አሰባሰብ ቅስቀሳ ላይ የተባበሩት ወጣቶችን፣ ሚዲያዎችንና ሌሎችንም ላደረጉት ቀና ትብብር ምሥጋናቸውን ያቀረቡት አስተዳዳሪው ይህ በጎ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።

በዓሉ ሁሉም ሲልም ከታላላቅ አባቶች ጀምሮ በጋራ የሚከበር በዓል በመሆኑ ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በጋራ ማክበር ይኖርብናል ማለታቸዉን ደሬቴድ ቦንጋ ቅርንጫፍ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *