





የኢፌዴሪ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ኢኖቬሽን እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ባለድርሻ አካላት በሣይንስ እና ቴክኖሎጂ በአዲሱ ፖሊሲ ይዘት እና ስትራቴጂ አተገባበር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ቦንጋ ከተማ ሰጥቷል።
የክልሉ ኢኖቬሽን እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛው ጋጊያብ በወቅቱ እንደገለጹት በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተዘጋጀው ፖሊሲ እና እስትራቴጂ በክልሉ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ተግባራዊ እንዲሆን ትኩረት ይደረጋል ብለዋል።
በዚህም ያሉ እምቅ የተፈጥሮ ጸጋዎችና ሀገር በቀል እውቀቶችና ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር በማስደገፍ የክልሉን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራሎ ያሉት የቢሮ ኃላፊው በዘርፉ ዓለም የደረሰበትን ለመድረስ የሚታዩ ክፍተቶችን ማረም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው ጋር እንደሚሰራም ገልጸዋል።
ስልጠናውን የሰጡት በኢኖቨሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የዘርፉ ካውንስሎችና የክልሎች ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ኑርልኝ ኮኩ እንዳሉት ስልጠናው በክልሉ የመንግስት አገልግሎቶቹን ድጅታላዝ ለማድረግና ጸጋዎችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ወደ ውጤት ለመቀየር ያግዛል ብለዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2030 በሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተለያዩ ፖሊሲዎች እና እስትራቴጂ በመቅረጽ ወደ ትግበራ መግባቱንም ገልጸዋል።
በዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተዘጋጀው ፖሊሲዎችና እና እስትራቴጂ አተገባበር ላይ የተሟላና የተጣራ ግንዛቤ ማሳደግ እንዲያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
አቶ ኑርልኝ ኮኩ በክልሉ ፖሊሲውና እስትራቴጂው ውጤታማ እንዲሆን የተቀናጀ አመራር በመስጠት እና ተግባራዊነትን በመገምገም ዘመኑ የደረሰበትን ለመድረስ በትኩረትና በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ስልጠናው የሀገር በቀል እውቀቶችና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በስፋት ለመጠቀምና ተደራሽነቱን ለማስፋት አቅም ይሆናል ነው የተባለው።
የመድረኩ ተሳታፊ አመራሮች እንዳሉት ክልሉ በግብርና ምርት፣በማዕድን አጠቃላይ በዕምቅ የተፈጥሮ ጸጋ ባለበት ቢሆንም ባለፉት ጊዜያት በቴክኖሎጂ ባለመደገፉ ውጤታማነት ሳይረጋገጥ ቆይቷል ብለዋል።
በዘርፉ የወጣውን የፖሊሲ ይዘትና እስትራጅ ተግባራዊ በማድረግ በክልሊ የሚገኙ ፀጋዎችን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰርና በማስደገፍ ወደ ኢኮኖሚ ለመቀየር እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በፍቅር ከበደ
