
በ1996 ዓ.ም ተቀርፆ ተግባራዊ የተደረገው የወጣቶች ብሄራዊ ፖሊሲ ክፍል አምስት ላይ ወጣቶች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የአካባቢ ጥበቃና ማህበራዊ አገልግሎት እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት ተሳትፈው እራሳቸውንና ማህበረሰባቸውን ሊጠቅሙ የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት እንደሚገባ በግልፅ ተቀምጧል፡፡
ይህንንም መሰረት በማድረግ በ2002 ዓ.ም የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በተቀናጀ አግባብ ለመምራትና ብዛት ያላቸው ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ እንዲሰማሩ ለማድረግ የሚያስችል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰታንዳርድን በማዘጋጀት የክረምትና የበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በተሰኙ ሁለት የስምሪት መርሐ-ግብሮች በርካታ ወጣቶች በአገልጎሎቱ ላይ በመሳተፍ በመንግስት እና በማህበረሰቡ ያልተሸፈኑ የልማት ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛል ፡፡
የበጎ ፈቃድ ስራዎችን አስመልክቶ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ቢሮ ኃላፊ ጋር ቆይታ አድርገናል ። ቃለ – ምልልሱ እንደሚከተለው ቀርቧል ፡፡
በቅድሚያ ለቃለ ምልልሱ ፈቃደኛ ስለሆኑ አመሰግናለሁ። እኔም አመሰግናለሁ!
መኮ :እንተዋወቅ ስምና ኃላፊነትዎን ቢገልጹልኝ ?

ወ/ሮ ራሔል ሌዊ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ መኮ: ከክልሉ ምስረታ ወዲህ ባለፉት ሶስት ዓመታት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አተገባበር ምን ይመስላል ?
ወ/ሮ ራሔል ሌዊ ከክልሉ ምስረታ በኋላ ባለፉት 3 ዓመታት እያደገ የመጣ የበጎ ፈቃድ አግልግሎት ስራዎች አሉን ለአብነት በ2014 የወጣቶች ተሳትፎ 408,286 በ2015 ወደ 599,593 ያደገ ሲሆን በ2016 ደግሞ ሌሎች ማህበረሰብን ጨምሮ 699,593 በጎ ፈቃደኞችን ለማሳተፍ ታቅዶ አሁን በተደረሰበት 527,105 ማድረስ ተችሏል፡፡
መኮ:_ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች በምን በምን ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ ሲፈጸም የቆየው?

ወ/ሮ ራሔል ሌዊ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ሰዉ ተኮር በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰሩ ይገኛሉ እንደክልል በዘንድሮ ዓመት በ 14 የስምርት መስኮች ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ (ችግኝ ተከላ) ለአረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች ቤት መስራት መጠገን ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸውን ሰበዓዊ ድጋፍ ማድረግ ማዕድ ማጋራት ፡ በችግር ዉስጥ ላሉ ህጻናት ከትምህርት ቤት ዉጭ እንዳይሆኑ የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰብ የአቅመ-ደካሞችን ማሳ ማረስ የአረም ቁጥጥርና ምርት ማሰበሰብ የከተማ ጽዳት ቦይዎችን ማጽዳት አነስተኛ ድልድይዎችን መስራት መጠገን ደም ልገሳ ዕና ሌሎችንም ስራዎች ትኩረት ተድርጎ እየተሰራ ይገኛል ፡፡
መኮ:_ የተገኙ አብነቶችን ሊጠቅሱልኝ ይችላሉ
ወ/ሮ ራሔል ሌዊ በአጠቃላይ ከላይ ተዘረዘሩትን መሰረት ተድርጎ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ባህል የማድረግ ስራዉ ዉጤት የተገኘበትና በአብዛኛው ዞኖች የበጎ ፈቃድ ማህበራት እየተደራጁ ያሉበት መልካም ጅማሮዎች አሉ

መኮ:_ ለአብነት ብለው ከጠቀሱዋቸው የበጎ ተግባር ስራዎች በተሻለ ደረጃ የተከናወነው የትኛው ነው?
ወ/ሮ ራሔል ሌዊ በአብዛኛዉ በሚባል ደረጃ የተሻለ አፈጻጸሞች ተመዝግበዋል ፡፡
መኮ:_ ወደ ኋላ የቀሩ ተግባራት ይኖሩ ይሆን? አዎ ከሆነ ምክንያቱን ቢያብራሩ።

ወ/ሮ ራሔል ሌዊ ወደ ኃላ ቀሩ የሚባሉት የሙያ አግልግሎት የስምሪት መስክ ያሉ ተግባራት ጅምር ስራዎች ቢኖሩም ጉድለት ያለባቸዉ ናቸዉ
መኮ:_ በዋናነት ሰው ተኮር ስራዎች ሲከናወኑ ከቆዩት ውስጥ በተለይ የአረጋውያን ቤት ዕደሳ ተጠቃሽ ነው። አፈጻጸሙን እንዴት ተመለከቱት? በየዓመቱ ያለውን አፈጻጸም እንዴት ይገልጹታል ?
ወ/ሮ ራሔል ሌዊ የአረጋውያን ቤት ዕደሳትን በተመለከተ በየአመቱ እየጨመረ የመጣ ሲሆን በተሻለ አፈጻጸም ያለበት ተግባር ነዉ፤ በ2014 አድስ ቤት 382 የተጠገኑ 296 በድምር 678 ቤቶች ፤ በ2015 አድስ ቤት448 ጥገና 398 በድምር 846 ቤቶች፤ በ2016 አሁን የተደረሰበት አድስ ቤት 434 ጥገና 227 በድምሩ 661 ቤት ደርሷል አስከ ማጠቃለያ 938 ቤት ለማድረስ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነዉ፡፡

መኮ:_ በዚህ የበጎ ተግባር ስራዎች የህብረተሰቡን ተሳትፎ ቢገልጹልን?
ወ/ሮ ራሔል ሌዊ በበጎ ተግባር የህበረተሰቡ ተሳትፎ እየጨመረ የመጣ ነዉ በ2014 የወጣቶች ተሳትፎ 408,286 በ2015 ወደ 599,593 ያደገ ሲሆን በ2016 ደግሞ ሌሎች ማህበረሰብን ጨምሮ 699,593 በጎ ፈቃደኞችን ለማሳተፍ ታቅዶ አሁን በተደረሰበት 527,105 ማድረስ ተችሏል፡
መኮ:_ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፏቸው እንዴት ይገለጻል ?
ወ/ሮ ራሔል ሌዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ካለማንም አነሳሽነት ከዉስጥ በመነጨ ፍላጎት ያለምንም ክፍያ የሚሰራ ስራ እንደመሆኑ የሁሉንም ባለድረሻአካላት ርብርብ የሚጠይቅ ነዉ እንደክልላችን ስራዉን በማስተባበርና በመምራት የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ ነዉ

መኮ:_ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከመንግስት ይወጣ የነበረን በጀት በእጅጉ ታድጓል። ሊጠቀስ ይችላል?
ወ/ሮ ራሔል ሌዊ በየዓመቱ የጠሰሩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች በገንዘብ ስተመን ከመንግስት ይወጣ የነበረዉን ወጪ ከማትረፍ አንጻር እየጨመረ መጥቷል በዚህም በ2014 ብር 254,506,700 በ2015 ብር 509,641,021 ያተረፍን ሲሆን በ2016 ደግሞ የተሸለ ለመፈጸም አቅደን እየሰራን እንገኛለን፡፡

መኮ:_ በቀጣይስ ይህንን አጠናክሮ ከማስቀጠል አኳያ የተያዘ ዕቅድ ካለ?
ወ/ሮ ራሔል ሌዊ ይህ ተግባር ሲሰራ ዋጋ የማይተመንለት ብዙ ስራዎችን ይዘን የምንሰራበት ስለሆነ ለአእምሮ ዕረፈት ለመንፈስ ዕርካታ የሚሰጥ እንደመሆኑ ብዙ አስተዋሽ ያጡ የሚታዩበት ትላንት ለሃገር ዋጋ የከፈሉ ዛሬ አቅም የከዳቸውን የሃገር ባለዉለታ አረጋዊያንን ሚንደርስበት ስራ እንደመሆኑ አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል፡፡
መኮ:_ለሰጡኝ ማብራሪያ ከልብ አመሰግናለሁ ።
ወ/ሮ ራሔል ሌዊ እኔም አመስግናለዉ!!
