የወረዳውን መሠረታዊ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ለመፍታት የህዝብን አቅም መጠቀም ይገባል። ሀብታሙ ካፍትን

Spread the love

የጊዲ ቤንች ወረዳ ልማት የሀብት አሰባሰብ ስራዎች ይፋዊ አጀማመር ዙሪያ በቤንች ሸኮ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን የተመራ የወረዳ አስተዳዳሪችና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች የወረዳውን የልማት ሥራዎች ጉብኝት አካሂዷል።

የጊዲ ቤንች ወረዳ በቤንች ሸኮ ዞን በለውጡ መንግስት ከተደራጁ ወረዳዎች ውስጥ አንዷ ናት።

ወረዳዋ 36 ሺህ ሄክታር ስፋት መሬት ያላት ሲሆን ወደ 100 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ያላት ወረዳ ነች።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን እንደተናገሩት በወረዳዎች በርካታ የህዝብ የልማት ጥያቄዎች መኖራቸው ይታወቃል ብለዋል።

በዚህም በጀት ከመንግሥት በቀመር የሚወርድና የህዝብን አቅም በማነቃነቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕምርታን ሊያመጣ በሚያስችል መልኩ ምላሽ መሥጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

ህዝብን በልማት ማስተሳሰር ከወረዳው አመራር ይጠበቃል ያሉት ዋና አስተዳዳሪ ልማቱን የህዝብ አጀንዳ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

አክለውም የወረዳው አመራር ጠንከር ብሎ በመግባት ወደ ራሳቸው ማየት አማራጭ የለሌው ጉዳይ ነው መሆኑንም አስገንዝበዋል።

አያይዘውም የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ከሌላ አካል የሚጠበቅ በጀት አለመኖሩንም ጠቁመዋል።

የመልማት ችግሮችን ለመፍታት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ወሳኝ ነው ብለው ዞኑም ማንኛውንም ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል ።

የጊዲ ቤንች ወረዳ አቶ አስቻለው አሠፋ የወረዳውን አጠቃላይ ገጽታ አብራርተው ወረዳው መሠረታዊ የመሠረተ የልማት ችግሮች መኖራቸውን ተናግረዋል ።

የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ብርሃኑ በበኩላቸው በወረዳው ስላሉ ምቹ ሁኔታዎችና ተግራቶች ዙሪያ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

በወረዳው የተገኙት የወረዳ አስተዳዳሪዎች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እንዳሉት የወረዳውን የልማት ስራ በህዝብ ንቅናቄ ማስተሳሰር እንደሚያስፈልግ አስረድተው የበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

በመድረኩ የዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን ፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎች ፣ የሁሉም መዋቅር የፓርቲ ኃላፊዎች ፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ፣ የክልሉ የመንግሥት ኃላፊዎች እንዲሁም ባለሀብቶች ተሳትፈዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *