
በአማራ ክልል ላይ ከየትኛውም መንግስት በላይ አሁን ያለው መንግስት በርካታ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ነው፡፡
በክልሉ ታላላቅ የመንገድ፣ የኢንዱስትሪ የቱሪዝም ልማቶች እየተከናወኑ ነው፡፡ በዚህም ክልሉን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
የፋሲል ቤተ-መንግስት እየታደሰ ነው፤ በዋና ዋና ከተሞች የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ነው፡፡
የመገጭ ግድብን 7 ቢሊዩን ብር መድበን ከበርካታ ዓመታት የግንባታ መቋረጥ በኋላ ቀን ከሌት እየገነባን ነው፡፡ ነገር ግን በክልሉ ልማት እንዳይከናወን ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎች አሉ፡፡ ይህን ተባብረን ማስቆም አለብን፡፡
የአማራ ህዝብ ማን እንደሚሰራለትና ማን እንደሚያወራለት ጠንቅቆ የሚያውቅ ጨዋ ህዝብ ነው፡፡ መንግስት ክልሉን የማልማት ስራውን አሁንም አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
