የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በይፋ ተጀመረ

Spread the love

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በቦንጋ ከተማ ተጀምሯል::

የምክክር መድረኩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በጋራ በመዘመርና ሐይማኖት አባቶችና ሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን በሂደቱም በክልሉ ከ57 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የወከሉ ተወካዮች እየተሳተፋ ይገኛሉ::

በምክክር መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ኢትዮጵያ ነፃናቷን ጠበቃ የኖረችው ብዙ ፈተናዎች ተሻግራ ለዚ መድረሷን ጠቅሰው ለዚህም የአባቶች ምክክር ከፍተኛ ድርሻ እንደለው ገልፀዋል፡፡

ሁላችንም እዚህ የተሰበሰብነው አንድ ነገር ጨንቆን ነው ያሉት ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በሀገራችን የማህበራዊ፣ ፖሊትካ እና በሌሎች መካፋፈል በመኖሩም ለዚህም ይህ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

ይህንን ዓላማ ለማሳካት መደማመጥ፣ መወያየት እና በመመካከር ዓላማችንን ለማሳካት ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ እንደገለጹት በየደረጀ በሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ምክንያቶች አለመግባባቶችና የሀሳብ ልዩነቶች ልፈጠሩ የሚችሉ አጋጣሚዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ችግሮች ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር በሚታይበት ጊዜ እንደየህብረተሰቡ ባህል፣ ልማድና ወግ መሠረት ጉዳዩን የሚመለከታቸው ሰዎች ሲሳተፉ የቆዩበት አግባብ መኖሩን ገልፀዋል ፡፡

ለዚህም እንደ ሀገር እየተደራረበ የመጠውን ወቅታዊና ውስብስብ ችግሮች በሰለጠነ መልኩ በውይይትና በምክክር ልምድ ተቀራርቦ መፍታት አስፈላጊ ነው ያሉት ኮሚሽነር ሙሉጌታ ።

የመድረኩ ተሳታፊ የህብረተሰብ ተወካዮች የጉዳዮን ፋይዳ በደንብ በመረዳት በደንብ በመወያየት ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸዉን አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ እንዳያቀርቡም ኮሚሽነር ሙሉጌታ አሳስበዋል።

ለመድረኩ መሳካት አጀንዳ ከመስጠት ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን አጠናክረዉ እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

ለ7 በሚቆየው መድረክ በአጠቃላይ ከ 2ሺህ 2 መቶ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች እና ባለድርሻ አካላትን ተሳታፊ ይሆናሉ::

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *