በክልሉ የስፖርት ዘርፍ ውጤታማነት ለማሳደግ ሁሉም የባለድርሻ አካላት ሚናቸውን ልወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ በክልሉ ካሉ ከሁሉም የስፖርት ፌዴረሽኖች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ በክልሉ የስፖርት ዘርፍ ውጤታማነት እንዲያድግና ህዝባዊ መሠረት እንዲይዝ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን ልወጡ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ስፖርት ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊና እድገትና ለህዝቦች ትስስር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ፋንታሁን ክልሉ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ቢሮው በዘርፉ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑንም አብራርተዋል።

የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፌ ጉባኤና የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ፀሀይ ዳርጫ በበኩላቸው ከስፖርት ፌዴረሽኖች አደረጃጀት ጋር ያለውን ማነቆ በመፍታት ፌዴሬሽኖች ሚናቸውን በሚገባ እንዲወጡ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

በክልሉ የስፖርቱን ዘርፍ ማስፋፋትና ማልማት የሁሉም ሀላፊነት ነው ያሉት የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አህመዲን አወል ፌዴረሽኖች የተቋቋሙበትና ዓላማ ከማስፈፀም አንፃር የሚታዩ ውስንኖቶችን መቅረፍ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በታዳጊ ስፖርተኞች ላይ በትኩረት መስራት በቀጣይ ክልሉንና ሀገርን የሚወክሉ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችልም አቶ አህመዲን አስረድተዋል።

በክልሉ ከማስ ስፖርት ውጤታማነት፣ ከታዳጊ ስፖርተኞች ማስልጠኛ ማዕከል፣ ከስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ጋር ተያይዞ የሚታዩ ማነቆዎችን በጋራ መፍታት እንደሚያስፈልግም ተጠቅሷል።

ለስፖርቱ ዘርፍ እድገት የባለሀብቶች ፣ የማህበረሰቡና የስፖርት ማህበራት ተሳትፎና ድጋፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም ተገልጿል።

ክልሉን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተገቢው የሚወክል ክለብ እንዲደራጅ በቅንጅት ልሰራ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆንበቅርቡ በጃፓን በተደረገው የጅምናስትክ ስፖርት ኢትዮጵያን የወከለው የደቡብ ምዕራብ ክልል ተወካይ በክልሉ በስፖርት ዘርፍ አስቻይ ሁኔታዎች መኖሩን ያሳያል ብለዋል።

በመድረኩ የተሳተፉ በክልሉ ያሉ የ13 ፌዴረሽኖች ተወካዮችና የዞን ስፖርት መምሪያ ሀላፊዎች ለክልሉ ስፖርት ዘርፍ እድገትና የዘርፉ ተጠቃሚነት ሚናቸውን በአግባቡ እንደሚወጡ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *