
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ቀን ብሄራዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት”! በሚል መሪ ቃል ሕዳር 22 የክልለሉ የብሄረሰቦች ምክር ቤት መቀመጫ በሆነቺው ቴፒ ከተማ ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል ፡፡
በሃገር አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል በክልሉ ሁሉም ዞኖች በተለያዩ ሁነቶች በደማቅ ሁኔታ የተከበረ መጥቷል ፡፡
ክልላዊ ማጠቃለያም በቴፒ ከተማ ህዳር 22/2017 ዓ/ም በተለያዩ ኩነቶች የሚከበር ሲሆን የወል ትርክቶችን መሠረት በማድረግ ጠንካራ፣ የበለፀገች እና ዘላቂ ሰላሟን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን በመገንባት ለቀጣዩ ትዉልድ ለማስተላለፍ ለብሄረሰቦች እውቅና የሚሰጠው በዓል መከበር ሚናው የጎላ ነው ፡፡
በቴፒ ከተማ 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ቀን “ሀገራዊ መግባባት ፤ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት”! በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች በተገኙበት በዓሉ የሚከበር ሲሆን ለዚሁ ስኬት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ተድርጓል ።
የብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ቀን እንደ ደቡብ ምዕራብ ክልል ለ3ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን ይህም ብሄር ብሔረሰቦች ያላቸውን ቱባ ባህላቸውንና ዕሴቶቻቸውን በአደባባይ እንዲያስተዋውቁ ዕድል የሚሰጥ ነው ፡፡
የብሔር ፣ብሔረሰቦችን እና ህዝቦች ቀንን ስናከብር ክልላዊ የመልማት ጸጋዎቻችንን እውን በማድረግና ዘላቂ ሰላማችንን ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ ሊሆን ይገባል ፡፡
እንደ ሀገር የ19ኛው ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ በታላቅ ድምቀት በተለያዩ ኩነቶች እንደሚከበር የሚጣወቅ ሲሆን የክልላችን አምባሳደሮችም በክብረ በዓሉ ተገኝተው የበዓሉ ተሳታፊ ይሆናሉ ቱባ ባህላቸውን ለዓለም የሚያስተዋውቁበትን ዕድል በተገቢው ይጠቀማሉ ፡፡
እንኳን ለ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች ህዝቦች ቀን በሰላም አደረሳችሁ ፡፡
