የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 ዓም የክረምት ወራት በጎ አገልግሎት አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ፡፡

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 ዓም የክረምት ወራት በጎ አገልግሎት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ባሻ እንደገለጹት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ አዎንታዊ አበርክቶ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ዘርፉ በርካታ ተልዕኮዎችን ያነገበና የተለያዩ አደረጃጀቶችን የሚያንቀሳቅስ በመሆኑ ዘርፉ የነገበውን ተልዕኮዎችን ከግብ ለማድረስ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዚህም የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀቶች ፣የሲቪል ማህበራትና ድርጅቶች፣ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ከበጎ አድራጎት ከሚመለከታቸው ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ዜጎች ከመደራጀት ነጻነት ጋር ተያይዞ ነጻነትን በህግ ላይ ቢቀመጥም ከተግባራዊነት አኳያ ችግር እንደነበረበት ይታወቃል ሲሉ ጠቅሰዋል።

ከለውጡ በኃላ ማህበረሰቡ በፈለገው ዓላማ ላይ ህጉን ተከትሎ ተደራጅቶ በጎ አላማዎችን የሚፈጽሙ የሚያችሉ ከዚህ ቀደም የነበሩ አሳሪ ህጎችን መልሶ በማስተካከል ሚናቸው ከፍ እንዲል ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል የተለያዩ ምቹ ምህዳር በመፈጠር ረገድ ህግንም ጭምር በማሻሻል ሁኔታዎች ተፈጥረዋል ብለዋል።

በዚህም ዛሬ ለምንመኘውና ለጀመርነው ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ አዎንታዊ አበርክቶ እያደረገ የሚገኝ ዘርፍ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ፓርቲያችን ብልጽግና የበጎነት እሳቤ ልዩ መገለጫው በመሆኑ በጎነት ወቅታዊ ሳይሆን ሁልግዜ የሚሰራ ተግባር መሆኑን የገለጹት አቶ ግርማ በክረምት ወራት በበጎ አገልግሎት የተከናወነት ተግባራት በበጋ ወቅት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በዓፈጻጸም ግምገማው የዘርፉ ተልዕኮ እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ሰፉ ያለ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

በመድረኩ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ባሻ ፣ የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ ፣የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች፣የዞን የወረዳና የከተማ አስተዳድር የወጣቶችና ሴቶች ሊግ እንዲሁም የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት አመራሮች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *