




የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የማብሰሪያ እና ሥራ ማስጀመሪያ መርኃግብር በግራንድ ኤሊያና ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።
በመርኃ ግብሩ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር እና የፋና ሚድያ ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የሚዲያው አመራሮች የድርጅቱ ሰራተኞች፣ ተባባሪ አዘጋጆች፣ የሚዲያው አጋሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቀድሞ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ተዋህደው የመሰረቱት ግዙፍ የሚዲያ ተቋም ነው።
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን
