ኢትዮጵያ አንድነት የሚገለጥባት ድንቅ ምድር ናት – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Spread the love

ኢትዮጵያ አንድነት የሚገለጥባት ድንቅ ምድር መሆኗን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለ19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ህብር የሀገሪቱን አንድነት እንደማይሸረሽረው ፤ ሀገራዊ አንድነቱም የኢትዮጵያን ህብራዊነት እንደማይጠቀልለው አውስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ “ህብራዊነቷ ጌጧ፣ መልኳ፣ ጸጋዋ፣ ሐብቷ ነው ፤ አንድነቷ ደግሞ ኃይሏ፣ ጉልበቷ፣ ዐቅሟ ነው” ብለዋል፡፡

ሀገሪቱ ያላትን ሐብት፣ ጸጋ እና ዕድል ፤ የበለፀገች፣ ጠንካራ እና የታፈረች ህብረ ብሔራዊት ሀገር ለመገንባት መጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ይህን በተሻለ ሁኔታ ለማድረግም በወሳኝ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኀበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *